በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ለፋብሪካው አገልግሎት ላይ የሚውል ስንዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Wolaita Sodo Flour and Bread Factory (የወላይታ ሶዶ ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ለፋብሪካው አገልግሎት ላይ የሚውል ስንዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የምትችሉት በሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና ለ2018 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ከዚህ ፊት ላከናወናቸው ተመሳሳይ ሥራዎች (አገልግሎቶች) ከአሠሪው አካል የመልካም ሥራ ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች በተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ ብር) በወላይታ ሶዶ ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ አካውንት ቁጥር 1000531817552 ገቢ ያደረጉበትን ስሊፕ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቢሮ ይገኛል።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም፤ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡ 16ኛው ቀን የበአላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና የ50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በታወቀ ባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ርክክብ የሚፈጸምበት ቦታ በወላይታ ሶዶ ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ይሆናል፡፡
- የወላይታ ሶዶ ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲሁም በማንኛውም ጊዜ የማራዘም ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 0913635285/0926349286/ ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወላይታ ሶዶ ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ
