Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ
  • Address ደቡብ ወሎ ዞን : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0331118571
  • Website
  • Deadline29 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityየአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 2%
  • opening date2025-12-29 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

በደቡብ ወሎ ዞን በእሪኩም፡ታቦር እና የወል ዩኒየኖች ለ2018/2019 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በዩኒየኖች ስር ባሉ 210 መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ደ/ወ/ግ/001/2018

 

በደቡብ ወሎ ዞን በእሪኩም፡ታቦር እና የወል ዩኒየኖች ለ2018/2019 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በዩኒየኖች ስር ባሉ 210 መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች

  1. የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር/ቢሮ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድና የዘመኑን የመንግስት ግብር ለመክፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  2. የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት /ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  3. ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሽከርካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነና ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ፤
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ተሸከርካሪ ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
  5. የተሽከርካሪ ዝርዝር /ተ.ቁ፣ የሰሌዳ ቁጥር፣ የመኪናው ዓይነትና የመጫን አቅም (የሚያስረዳ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2018 ዓ.ም ወቅታዊ የታደሠ ምዝገባ ፊቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  6. ከላይ ከ 1 እስከ 5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው
  7. ተጫራቾች ጨረታውን የሚጫረቱት በመሰረታዊ ማህበር ሆኖ በማጓጓዝ ሂደት ላይ የጸጥታ ችግርም ሆነ ሌላ ችግር ካጋጠመና የማራገፊያ ጣቢያ ወይም ቦታ ቅያሬ ከተደረገ ክፍያ የሚፈጸመዉ በተራገፈበት መሰረታዊ ማህበር ጨረታ ባሸነፈበት ዋጋ ይሆናል
  8. ማንኛውም ተጫራች የወቅቱን ገበያ ዋጋ ግምት ውስጥ አስገብቶ ዋጋ ከሞላ በኋላ እና ማሸነፉ ተነግሮት ውል ከወሰደ በኋላ ምንም አይነት ዋጋ ጭማሪ ይደረግልኝ ብሎ ጥያቄ ማቅረብ አይችልም
  9. የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት፣ መጠን የቦታ እርቀት በኪ/ሜትር ከጨረታ ሰነዱ ያገኛሉ
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ዩኒየን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ ማግኘት ይቻላል፣
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ /ሲ.ፒ.ኦ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው።
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በሶስቱም ዩኒየኖች ስም ደ/ወሎ ዞን ግ/መምሪያ የግብ/ግብ/አቅ/ገጠር ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 13 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ከ16ኛው ቀን ማለትም 20/04/2018ዓ.ም እስከ 4፣00 ሰዓት ድረስ በመምረያው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በማስገባት የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈተው በእለቱ 20/04/2018ዓ.ም በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  13. ጨረታውን ያወጣው የደቡብ ወሎ ዞን የግ/ግ/ኣ/ዝ/ፋይናንስ ቡድን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግብርና ግብአት አቅርቦትና ገጠር ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 እና 13 ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0331118571 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ

 

Save Tender