የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት እስቴሽነሪ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሰሜን ሽዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት እስቴሽነሪ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሱ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር መለያ ቁጥር /Tin no/ ያላቸው
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዛ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 - 4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶሰት መቶ ብር/ ተጫራቹ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ ቢድ ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሞ/ወ/ወ/የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በወጣበት በ15ኛው ቀን ዓ.ም 11፡30 ይዘጋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በሞ/ወ/ወ/በሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 0116250497 0921127777 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
ይህ ማስታወቂያ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድና በአላት ቀን የሚውል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀናት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
