በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ አገልግሎት የሚውል የመኪና ጎማ ግዥ ለመግዛት ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Afar Regional Health Bureau (በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ አገልግሎት የሚውል የመኪና ጎማ ግዥ ለመግዛት ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የመኪና ጎማ ግዥ
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዚህ ግልፅ ጨረታ የሚወዳደሩ አቅራቢ ድርጅቶች በ2018 ዓ.ም በጀት አመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምዝገባ ሠርቲፍኬት ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሀሳብ ኦርጅናሉን በአንድ ፖስታ ኮፒውን በአንድ ፖስታ የተጫራቾቹ ስምና ፊርማ አድራሻ በግልፅ ተፅፎባቸው ሁለቱም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጎ በሰም የታሸገ ፖስታ መቅረብ ሲኖርበት ፖስታዎቹን በተወሰነው ጊዜና ሰዓት በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ በግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ ስራ ሂደት ህንጻ ቁጥር 1 ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሀሳብ ቢሮው ለመግዛት የፈለገውን እቃዎች ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ የመወዳደሪያ ሰነድ ማቅረብ ወይም የመጫረቻ ሰነድ ማምጣት ግዴታ አለባቸው።
- የሚገዙት እቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላል።
- ማንኛውም የጨረታ ተወዳዳሪ ለሚያቀርባቸው እቃዎች ቫት ሳይጨምር የጠቅላላ ዋጋውን 1% የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ቼክ (CPO) ከመወዳደሪያ ሃሳብ ማቅረቢያ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በግልፅ ጨረታ በመውሰድ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ በግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ደጋፊ ስራ ሂደት ህንጻ ቁጥር 1 መውሰድ ይችላሉ።
- የተዘጋጀው ጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ለ11 ተከታታይ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ድረስ ግልፅ ጨረታ ገዝተው በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ በግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ደጋፊ ስራ ሂደት ህንጻ ቁጥር 1 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ሰነዱን ገዝተው በመሙላት እና በማዘጋጀት ኦርጅናል የመወዳደሪያ ሀሳብ ዶክመንታችሁን በአንድ ፖስታ ውስጥ በሰም በማሸግ ኮፒውን በሌላ ፖስታ ውስጥ በሰም በማሸግ በማስገባት ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ አድርጎ በሰም አሽገው ለዚሁ ግዥ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ቢሮው ሊገዛው ያቀረበዉ የእቃ ዝርዝር ተጫራቾቹ በከለር የታተመ ስዕላዊ መግለጫ ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ሻጭ ንብረቱን ንብረት ክፍል ድረስ ወስዶ ካስረከበ በኋላ በስሙ ሞዴል 19 አስቆርጦ ሂሳብ ክፍል ወስዶ ሂሳቡን ማወራረድ አለበት።
- የጨረታው መክፈቻ ጊዜ ቀን የጨረታውን መክፈቻ ፕሮግራሙን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መክፈቻ ሂደት አያስተጓጉልም።
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለጎዎት የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጤና ጥበቃ ቢሮ በግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ደጋፊ ስራ ሂደት
በስልክ ቁጥር 033-666-0015 ደዉለው ይጠይቁ፡፡
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
