Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በወረባቦ ወረዳ የቢስቲማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
  • Address ደቡብ ወሎ ዞን በወረባቦ ወረዳ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0906425432
  • Website
  • Deadline25 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየሽያጭ መነሻ ዋጋ 5%
  • opening date2025-12-25 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working , Vehicle Spare Parts

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በወረባቦ ወረዳ የቢስቲማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት አመት በወረባቦ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት ስር የቢስቲማ ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሰጡና ተመላሽ የተደረጉ የመኪና እቃዎች ሎት፤1 እስቲል ብረቶች ሎት፤2 በሎት ድምር አወዳድሮ አሸናፊዎችን በመለየት መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በወረባቦ ወረዳ የቢስቲማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ


 

የግልጽ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በወረባቦ ወረዳ የቢስቲማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት አመት በወረባቦ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት ስር የቢስቲማ ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሰጡና ተመላሽ የተደረጉ የመኪና እቃዎች ሎት፤1 እስቲል ብረቶች ሎት፤2 በሎት ድምር አወዳድሮ አሸናፊዎችን በመለየት መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች አግባብ ያለው መለያ ማለትም የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ኦርጅናል፤ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ እንዲሁም ፍቃድ ካለ የንግድ ሥራ ፈቃድ በአንድ ላይ በፖስታ አሽገው ስም እና ፊርማ የድርጅቱ ማህተም ካለዎት ማህተም ከሌለ ፊርማ እና ስልክ ቁጥር በማስፈር ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
  3. የሚሸጡ እቃዎችን አይነት እና ዝርዘር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
  4. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በቢስቲማ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 1 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ 06 /04/ 2018 ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ከ 06/04/2018 ዓ.ም እስከ 16ኛው ቀን በ 16 /04 /2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በእያንዳነዱ ሎት በመለየት በፖስታ ማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በወ/ወ/ቢ/ጤ/ጣቢያ በግዥ እና ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ 16 /04 /2018 ዓ.ም ከጧቱ 5፡00 ይዘጋል
  7. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ 16 /04/2018 ዓ.ም ከጧቱ 5፡30 ተጫራቾች ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በተጫራቾች ፊት በወረባቦ ወረዳ ቢስቲማ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 1 በግልፅ ይከፈታል።
  8. አሸናፊው ተጫራች ያሸናፋቸውን እቃዎች በተጠየቀው መሰረት ውለታ በመውሰድ እና ሙሉ ክፍያ በወረባቦ ወረዳ ቢስቲማ ጤና ጣቢያ አካውንት ቁጥር በማስገባት /በመክፈል/ ያስገቡበትን የባንክ አስሊፕ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን የሽያጭ መነሻ ዋጋ 5% በእያንዳንዱ ሎት በመለየት ማለትም ለሎት 1 ብር ፤ ለሎት 2 ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ ሲ.ፒ.ኦ /ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ መሂ 1 በመቁረጥ ከጨረታ ፖስታው ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. በጨረታ ሰነድ ላይ ከሰፈሩት የውል ቃሎች እና ሁኔታዎች ጋር መሰረታዊ ልዩነት ያለው ሀሳብ ማቅረብ ከጨረታው ተሳታፊነት ያሰርዛል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
  12. በነጠላ ዋጋ ላይ ሆን ተብሎ የተጋነነነ ስርዝ ድልዝ መኖር ከጨረታ ተሳታፊነት ያሰርዛል፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጨረታ ተጨማሪ ማስረጃ ቢያስፈልጋቸው 0906425432/ ወይም በግንባር በመቅረብ ወይም በስራ ሂደቱ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. የጨረታው መክፈቻ ቀን የበአል ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ከገጠመ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  15. ተመላሽ የመኪና እቃ መሸጫ መነሻ ዋጋ በኪ.ግ 51.25 ብር የኪ.ግ ብዛት 56.8 ጠቅላላ ብር 2911 እስቲል ብረት መነሻ መሸጫ ዋጋ 64 ብር እስቲል ብረት የኪ.ግ ብዛት 1545 ጠቅላላ ብር 98,880 በአጠቃላይ ድምር 98,936.8 (ዘጠና ስምንት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ስድስት ብር ከሰማኒያ ሳንቲም) መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

 

የቢስቲማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ

 

Save Tender