የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ባህልና ስፖርት ቢሮ የጂንካ ስፖርት ማበልፀጊያ ማዕከል የስፖርተኞች ቀለብ ምግብ ለመመገብ የሚፈልጉ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለማሠራት ይፈልጋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ /ጂንካ/
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ባህልና ስፖርት ቢሮ የጂንካ ስፖርት ማበልፀጊያ ማዕከል የስፖርተኞች ቀለብ ምግብ ለመመገብ የሚፈልጉ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለማሠራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግሥት ግ/ን/አ/ኤ/ድረ ገጽ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣የቲን የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ/ሲፒኦ/ ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ፣
- የጨረታ አሸናፊ 50% የጨረታ ዋስትና ማስያዝ አለበት፣
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ/ 15/ አሥራ አምስት የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ በ15 ቀናት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፣
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህገዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጐ በዛኑ ቀን በ10፡00 ሰዓት ይከፈታል፣
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ቢሮው ጨረታውን የመከፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ /ጂንካ/
ለበለጠ መረጃ በስልክቁጥር 046-77-52-968 ደውሎ ማረጋገጥ ይችላል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ /ጂንካ/
