Tender Detail

Tender Details

  • Company Southwest Education Bureau (የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ)
  • Address ታርጫ ከተማ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0473450715
  • Website
  • Deadline28 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Security50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-28 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Food And Beverage , Merchandise

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ ለዳውሮ ዞን ዛባጋዞ ወረዳ እና ለምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ምገባ አገልግሎት የሚውል ያልተፈጨ በቆሎ ፣ የውጭ ሩዝ ፣ ቦሎቄ ፣ የምግብ ዘይት እና ጨው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Southwest Education Bureau (የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር - ት/ቢ/ግ/ጨ/- 02/18

 

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ ለዳውሮ ዞን ዛባጋዞ ወረዳ እና ለምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ምገባ አገልግሎት የሚውል ያልተፈጨ በቆሎ ፣ የውጭ ሩዝ ፣ ቦሎቄ ፣ የምግብ ዘይት እና ጨው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች እንዲወዳደሩ ይጋበዛል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
  4. በአቅራቢነት የተመዘገቡ
  5. ከዘመኑ ግብርና ታክስ ነጻ የሆኑ
  6. የሚቀርቡት እህሎች የግብርና ምርቶች ጥራት ያላቸውና የፋብሪካ ውጤቶች የጥራት ደረጃቸው የተረጋገጡ መሆን አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ታርጫ ከተማ ግ/ፋ/ን አስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በኢን.ባ በቢሮው ሂሳብ ቁጥር 1000453714528 በማስገባት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  8. ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ C.P.O. ፣ በካሽ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ህጋዊ የንግድ ማስረጃ ፣ CPO እና ቴክኒካል ሰነድ ዋናና ኮፒ ለየብቻ በሁለት ፖስታ፣ የዋጋ ፖስታ ዋናና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  11. ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። እንዲሁም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክልሉ ትምህርት ቢሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል።
  12. በመክፈቻው ዕለት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል። ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግዎ:- በስልክ ቁጥር 0473450715 መጠየቅ ይችላሉ።

 

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ

 

Save Tender