የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የመጀመሪያ ዙር የህዝብ ሽያጭ ዝግጁነት ምክር አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ምክር አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- ECMA/NCB/12/2018
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የመጀመሪያ ዙር የህዝብ ሽያጭ ዝግጁነት ምክር አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ምክር አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከባለስልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ክፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንስና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ክሊራንስ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን፤ እንዲሁም በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሰነደ መዋለንዋይ ኢቭስትመንት አማካሪ ፍቃድ ያገኙ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ሰአት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለı5 ቀናት ብቻ ነው።
- ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል።
- አሸናፊው ተጫራች የምከር አገልግሎቱ በተፈለገ ጊዜ ሁሉ በራሱ ትራንስፖርት ባለስልጣኑ ዋ/መ/ቤት ወይም የምክር አገልግሎቱ በሚካሄድባቸው ሌሎች ቦታዎቸ ሁሉ የመገኘት እና የምክር አገልግሎቱን የመስጠት ሃላፊነት አለበት።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያነት የብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ጨረታው ታህሳስ 13 ቀን 2018 ከሰዓት በ9:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በ9:30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሸ ይከፈታል።
- በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።
- ባለስልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚጎ ገባ ብሎ ባሰው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
ምናዩ ኮርፖሬት ቢሮ ፓርክ፣ ክ/ከተማ ቂርቆስ፣ ወረዳ 9 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ 011-5-57-83-27 ኢሜል: Procurement@ecma.gov.et
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት
