በደቡብ ወሎ ዞን የመካነ-ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ያለ ሕንፃ ለመቀባት የግብአት (ቀለም) እና ሙያውን በአሸናፊ ድርጅት የሚሸፈን ሆኖ ውስጡንም ውጩንም በኦርጅናል ቀለም ለመቀባት (ለማደስ)፣ ማቴሪያል ችሎ የማህበረሰብ አቀፍ መድኃኒት ቤት /community pharmacy/ ግንባታ እና የህክምና እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው/ላት/
- የዘመኑን ግብር የከፈለ /ለች/
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ /ነች/
- ጨረታው የሚከናወነው በሎት ነው
- ሎት 1. ማቴሪያል ችሎ እድሳት ማድረግ
- ሎት 2. ማቴሪያል ችሎ የማኅበረሰብ አቀፍ መድኃኒት ቤት /community pharmacy/ ግንባታ
- ሎት 3. የህክምና እቃዎች
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /መቶ ብር/ እየከፈሉ ከሆስፒታሉ ዋና ገንዘብ ያዥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ድምር ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡
- የሆስፒታሉን እስፔስፊኬሽን መቀየር አይቻልም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል 16ኛው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የሕዝብ በአላት ቀን ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታውን መክፈት ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0914344306/0934370254/0949910998 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአብክመ ጤና ቢሮ የመካነሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል የግዥና ፋይናንስ ቡድን