Tender Detail

Tender Details


በፌዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ማሰ/ተቋም በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ለማሰ/ተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የምግብ እህሎች፣ አትክልቶች፣ እንቁላል እና የበሬ ሥጋ የተለያዩ የስፖርት ትጥቆች ቶርሽን ጫማ እና ሲቪል አልባሳት ግዥ በማስፈለጉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ማሰ/ተቋም


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ማሰ/ተቋም በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ለማሰ/ተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የምግብ እህሎች፣ አትክልቶች፣ እንቁላል እና የበሬ ሥጋ የተለያዩ የስፖርት ትጥቆች ቶርሽን ጫማ እና ሲቪል አልባሳት ግዥ በማስፈለጉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከሥራው ጋር የተገናኘ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው የአገር ውስጥ የድጋፍ ደብዳቤ ከገንዘብ ሚ/ር የሚሰጠውን የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬትና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ተጫራቾች የጨረታ መመሪያና የዕቃ ዝርዝር መግለጫ የሆነውን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ከአ/አበባ በደብረ ብርሃን መስመር 63 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ በስተቀኝ በኩል በሚገኘው የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፖሊስ ማሠ/ተቋም ሂሳብና በጀት ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት መግዛት የምትችሉ ሲሆን፡-

ተ.ቁ

 

የዕቃው ዓይነት

 

ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት

 

1

 

የተለያዩ የምግብ እህሎች፣ አትክልቶች፣ ዕንቁላል እና የበሬ ሥጋ ግዥ

 

ታህሳስ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 5:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።

 

2

 

የተለያዩ የስፖርት ትጥቆች ቶርሽን ጫማ እና ሲቪል አልባሳት ግዥ

 

ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።

 

 

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሲፒኦ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ/ ብር ከኢትዮጵያ ንግድ በባንክ ተረጋግጦ በሚሰጥ (CPO) በማሠራት የጨረታ መወዳደሪያ ፖስታ ውስጥ በማስገባትና በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚቀርበው የጨረታ ሠነድ በአማርኛ መሆኑን እየገለጽን መ/ቤቱ የተሻለ አመራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናሳስባለን።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፦ 011 672 0000 እና 09 20 16 91 44 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በቀድሞ ስሙ በአሌልቱ ወረዳ ፍቼ ገሊላ

 

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ ማሰ/ተቋም

Save Tender