በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ተሽከርከሪዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የግልፅ ጨረታ ቁጥር 03/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ተሽከርከሪዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
በግልፅ ጨረታ ቁጥር 03/2018 በ13/04/2018 ዓ.ም ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ለጨረታ የቀረበውን ተሽከርካሪዎችን ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች ፡-
- ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ዲጅታል /ብሔራዊ መታወቂያ ያለው
- ለጨረታ የቀረበው ተሸከርካሪ ሲሆን የሚገኘው ድረዳዋ ሙዲአኖ ገቢ በሚገኘው ተሽከርካሪ መጋዘን ውስጥ ነው።
- የተሽከረካው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የሆነ ሰው በጨረታ መሳተፍ አይችልም።
- በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለጸው መሰፈርት መሠረት ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከአርብ 03/04/2018 ጀምሮ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሰነዱን በመግዛት እና ሪሲት በመውሰድ ተሽከርካሪው በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል።
- ተሽከርካሪውን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
- ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ድረዳዋ ሙዲአነኖ የሚገኘው ገቢ ውስጥ ነው።
- ተጫራቾች በተሽከርካረው የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ተሽከርካሪውን ለመግዛት ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ 5% በንግድ ባንክ የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ የሞሉትን የጨረታ ሰነድ እና ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በማያያዝ በዕለቱ በፖስታ ውስት በማሸግ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 3:45 ድረስ በድረዳዋ ሙዲአነኖ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ከጠዋቱ 3:50 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድሬዳዋ ሙድአኖ ጉምሩክ ለጨረታ በተዘጋጀው ቦታ ሳጥኑ ይከፈታል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆኑ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ተሽከርካሪ አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል።
- ከላይ በተራ ቁጥር 12 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ተሽከርካሪውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረት ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለሥልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
- የጉምሩክ ኮሚሽን ድ/ደ/ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 15 46 09 70 (09 12 88 57 46) መደወል ይቻላል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
