Tender Detail

Tender Details

  • Company ዴኮማ ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒዬን
  • Address ቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ አደባባዩ ጋር ከፍ ብሎ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0970380799
  • Website
  • Deadline25 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Security50,000 /ሃምሳ ሺህ/
  • opening date2025-12-26 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

የዴኮማ ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒዬን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቡርጅ ዞን ለሚገኙ አርሶ አደሮች በያዝነው 2018/2019 ምርት ዘመን ሶያማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘኖች ለሰብል አብቃይ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ጣቢያዎች በበልግና በመኸር የአፈር ማዳበርያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

ዴኮማ ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒዬን


 

የደረቅ ጭነት ማመላለሻ

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018

 

የዴኮማ ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒዬን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቡርጅ ዞን ለሚገኙ አርሶ አደሮች በያዝነው 2018/2019 ምርት ዘመን ሶያማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘኖች ለሰብል አብቃይ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ጣቢያዎች በበልግና በመኸር የአፈር ማዳበርያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከድርጅቱ የማረገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ በመውሰድ ለመጓጓዝ የሚፈለገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠር መንገድ በአማካይ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልተው በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

በዚሁ መሠረት-

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን የግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃድ ያሳደሰ እንዲሁም የግብርከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፤
  2. ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  3. ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የስራ ዘርፉ ተሰማርቶ ሥራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈጻፀም ማቅረብ የሚችል፤
  4. የጨረታ ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ መዋቀር ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይቻልም፤
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /cpo/ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈፀሙ በፊት ያሸነፈበትን ጭነት የማጓጓዣ ዋጋ 10% በቅድሚያ ያስዛል፡፡
  7. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር ቢያንስ 200/ሁለት መቶ/ ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪኖችን የሰሌዳ ቁጥር፤ የመኪና አይነትና የመጫን አቅም /የሚያስረዳ ፊቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ/ ከደኮማ ሁለጉበ ህብረት ሥራ ዩኒዬን ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. የጨረታውን ሰነድ በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  10.  ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒዬን ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
  11.  ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው::

 

አድራሻ፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ አደባባዩ ጋር ከፍ ብሎ

ስልክ፡- 0970380799/0972629414/0954796833

 

ዴኮማ ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒዬን

 

Save Tender