Tender Detail

Tender Details

  • Company ቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 12 ፋይናንስ ፅ/ቤት
  • Address ቦሌ ቡልቡላ ከሳሪስ አቦ 3ኪ.ሜ ገባ ከቦሌ ሚካኤል 4ኪ.ሜ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ትንሹ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 26 78 33 34
  • Website
  • Deadline25 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-12-26 00:00:00
  • Categories Home Appliance And Supplies , Machinery , Electronics Materials

የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመርያ ደረጃ ቦሌ ምድብ ችሎት የመዝገብ ቁጥር 112896 በቀን 25/03/2018 ዓ.ም በፍርድ ባለመብት አቶ አህመድ ከድር እና የፍርድ ባለ እዳ አቶ መሀመድ ሰኢድ መካከል ባለው የፍተሐብሄር ክርክር ጉዳይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደርና ፋይናንስ ፅ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የቤት መገልገያ እቃዎችን በፍርድቤት ትእዛዝ መሰረት በጨረታ አወዳደሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 12 ፋይናንስ ፅ/ቤት


 

ግልፅ የእቃ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የእቃ ሽያጭ መለያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም

 

የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመርያ ደረጃ ቦሌ ምድብ ችሎት የመዝገብ ቁጥር 112896 በቀን 25/03/2018 ዓ.ም በፍርድ ባለመብት አቶ አህመድ ከድር እና የፍርድ ባለ እዳ አቶ መሀመድ ሰኢድ መካከል ባለው የፍተሐብሄር ክርክር ጉዳይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደርና ፋይናንስ ፅ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የቤት መገልገያ እቃዎችን በፍርድቤት ትእዛዝ መሰረት በጨረታ አወዳደሮ መሸጥ ይፈልጋል።  ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡

  1. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

 

የሚሸጡ እቃዎች ዝርዝር ፡-

 

ተ.ቁ

የእቃዎቹ ዝርዝር

የእቃዎቹ መነሻ ዋጋ

1

ባለ 16 ኪ.ግ ኤልጂ የልብስ ማጠብያ ማሽን

55,000

2

ባለ 2 በር ሳምሰንግ ፍሪጅ

70,000

3

ባለ 55 ኢንች ሳምሰንግ ከርቭድ ቴሌቭዥን

50,000

 

  1. ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ትንሹ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ አስ/ፋይናንስ ጽ/ቤት በአካል እየቀረቡ መውሰድ ይችላሉ
  2. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ትንሹ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ አስተዳደር እና ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ታሽጎ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 2፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  4. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ በእለቱ ገንዘቡን በክከፈል እቃዎችን መረከብ ይችላሉ
  5. ተጫራቾች ባሸነፉት ዋጋ መሰረት እቃወችን በ3 ቀን ውስጥ የመረከብ ግዴታ አለባቸው። ይህ ሆኖ ካልተገኘ ወደ 2ተኛው አሸናፊ ተጫራች እናልፋለን።
  6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡-

ቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር እና ፋይናንስ ጽ/ቤት ቦሌ ቡልቡላ ከሳሪስ አቦ 3ኪ.ሜ ገባ ከቦሌ ሚካኤል 4ኪ.ሜ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ትንሹ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ።

ለበለጠ መረጃ በቢሮ ስልክ ቁጥር 09 26 78 33 34

ማሳሰቢያ፡- በመጨረሻም የጨረታ ሳጥን የሚገኘበት ቦታ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ።

 

ቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 12 ፋይናንስ ፅ/ቤት

Save Tender