በኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች ጎማ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/EC/FP/NCB/08/2018
በኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች ጎማ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደርይችላሉ።
ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፣
ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የካ ከ/ከ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ግዥ ቢሮ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ዕቃዎችንና አገልግሎቶች በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/EC/FP/NCB/08/2018 የሚል ምልክት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
የአቅርቦት ግዥ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታውመክፈቻ ቀንና ስዓት |
|
ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች ጎማ ግዥ
|
ሎት-1 500,000.00 |
ታህሳስ 13 ቀን 2018 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ታህሳስ 13 ቀን 2018 ከቀኑ 8፡05 ሰዓት
|
|
ሎት-2 ብር500,000.00 |
* ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
* ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251 116 73 21 98 መደወል ይችላሉ፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
