በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽህፈት ቤት ግ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ለ2018 ዓ.ም ለሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ ቱታ እና የደንብ ጫማ ቶርሽን እቃዎች አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2018
በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ለ2018 ዓ.ም ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
ሎት 1 የደንብ ልብስ የስፖርት ትጥቅ ቱታ እና የደንብ ጫማ ቶርሽን እቃዎች አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ፡- የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለውና ግብር የከፈለ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ያላቸው
- በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው ያላት
- የግዥ መጠኑ 200000.00 (ከሁለት መቶ ሺህ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ድርጅት እቃዎቹን ወረዳው ድረስ የሚያቀርብ እና ሂሳቡን በስሙ የሚያወራርድ ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅርብ አለባቸው።
- የሚገዙ የእታዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫዎች ለፕስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን አልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 09/02 ድረስ በመገኘት የማይመለስ ብር 200 ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋውን በመሙላት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ዘርፍ የጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው። ፅ/ቤቱ ናሙና በሚጠይቁ እቃዎች ላይ ናሙና ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆኑ።
- የጨረታ ሰነዱ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህንን ማስታወቂያ የያዘው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀን በአየር ላይ በመቆየት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል ።
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጨረታው በተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ40 ተከታታይ ቀን ይቆያል ።
- በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ፣ ማብራሪያ፣ ጥቆማ ወይም ቅሬታ ካለ በህጉና በአዋጁ መሰረት አልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 በአካል፣ በጽሁፍ ወይም በስልክ መጠየቅ ይችላል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 2150032/0032150009
የአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
