Tender Detail

Tender Details


የአብክመ ጤና ቢሮ ለ2018 በጀት አመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመኪና መለዋወጫና ጌጣጌጥ እና የህክምና መሳሪያ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

Amhara Health Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአብክመ ጤና ቢሮ ለ2018 በጀት አመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመኪና መለዋወጫና ጌጣጌጥ እና የህክምና መሳሪያ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ሰርተፍኬት የሚያቀርብ፡፡
  3. ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፍኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ 2% /በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዝ ።
  6. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በታሸገ ፖስታ በጤና ጥበቃ ቢሮ በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል/ በፋይናንስ ህንጻ በ16ኛ ቀን 8:30 ታሽጎ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆን በተከታታይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
  8. ለህክምና መሳሪያ ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የፋይናንሻል ሰነድ አርጅናልና ኮፒ እንዲሁም የቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ።
  9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  10. ቢሮው የግዥውን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል ቀርበው መግዛት ይቻላል።
  12. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ስለጨረታው መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ግዥ ክፍል ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582221127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
  14. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃዎች በራስ ወጭ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት ፡፡

 

የአማራ ብ/ክ/መ/ ጤና ቢሮ

 

Save Tender