Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለ2018 በጀት ዓመት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የእቃ ግዥ ጨረታ  ጭረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/ቁ/02/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለ2018 በጀት ዓመት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ሎት 1: - የደንብ ልብስ ግዥ

ሎት 2፡- የደንብ ልብስ ስፌት ግዥ

ሎት 3፡- አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ

ሎት 4፡- አላቂ የህከምና አቅርቦቶች ግዥ

ሎት 5፡- የምግብ አቅርቦት ግዥ

ሎት 6፡- ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች ግዥ

ሎት 7፡- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ግዥ

ሎት 8 የህከምና ዕቃዎች ጥገና፣ ለፕላንት፣ ለማሽነሪና ለመሳሪያ፤ እድሳትና ጥገና ለአንድ አመት ውል የሚፈረም ግዥ

ሎት 9፡- የጥገና ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ

ሎት 10፤- የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ

ሎት 11፤ የህከምና ቋሚ ዕቃዎች ግዥ

ሎት 12፡- የአጥንት ህክምና መሣሪያ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልግ ተጫራች፡-

1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፍቃዱን ያደሰ፣

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና፡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል!

3. የአቅራቢነት ማስረጃ ያለው፣

4. ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ስለ ግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሣተፍ የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1፡- የደንብ ልብስ ግዥ 10000.00 ብር

ሎት 2፡- የደንብ ልብስ ስፌት ግዥ 50000.00 ብር

ሎት 3፡- አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ 5000.00 ብር

ሎት 4፣ አላቂ የህከምና አቅርቦቶች ግዥ 300000.00 ብር

ሎት 5፡- የምግብ አቅርቦት ግዥ 5000.00 ብር

ሎት 6፡- ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች ግዥ 10000.00 ብር

ሎት 7- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ግዥ 5000.00 ብር

ሎት 8- የህከምና ዕቃዎች ጥገና፣ ለፕላንት፤ ለማሽነሪና ለመሳሪያ፤ እድሳትና ጥገና ለአንድ አመት ውል የሚፈረም ግዥ 5000.00 ብር

ሎት 9- የጥገና ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ 100000.00 ብር

ሎት 10- የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ 500000.00 ብር

ሎት 11፡- የህከምና ቋሚ ዕቃዎች ግዥ 500000.00 ብር

ሎት 12፡- የአጥንት ህክምና መሣሪያ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ 350000.00 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ፣ወይም ጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።

6. ተጫራቶች ናሙናዎቻቸውን ሰነድ ሲገዙ የተሰጣቸው መለያ ኮዳቸውን ሰጥተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ለአንድ የአቅርቦት ዓይነት እንድ ናሙና ብቻ ማቅረብ አለባቸው::

7. አሸናፊ ተጫራቾች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ከምችት (የራሱ ስቶከ) ያለውና፣ እቃዎቹን በራሱ ማጓጓዣ (ወጪ) እስከ ሆስፒታሉ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ አምጥቶ እና በራሱ ወጪ አውርዶ ማስረከብ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ መረጃቸውን እና፤ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት መምጣት ይኖርባቸዋል፤ የማይመለስ ብር200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋት 2፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በሆስፒታሉ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር አዲስ (በመኪና መግቢያ በር ገብቶ ወደ ግራ እጥፍ ብለው) በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኢንሼሎፕ የሎት ቁጥሩ፤ ሰነድ ሲገዙ የተሰጣቸውን መለያ ኮድ ፅፈው፣ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም መተው፤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከሎት 1 እስከ ሎት 10 ያሉት ጨረታቸው አንድ (1) ኢንቨሎፕ ነው፡፡ እንዲሁም ሎት 11 እና ሎት 12 የህከምና ቋሚ እቃዎች ግዥ እና የአጥንት ህክምና መሣሪያ tom of piraረታቸው ሁለት (2) እንቨሎፕ ሰሆን (ሎት 11 እና ሎት 12 በአራት ፖስታ በሁለት አርጅናል እና ሁለት ኮፒ) ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ አሽገው፣ ኦርጅናል እና ኮፒ ለይተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. ጨረታው 10 ቀናት የአየር ላይ ቆይታውን እንዳጠናቀቀ በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ እለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።

10. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው ሆስፒታላችን በሰጠው መሙያ ቅጽ ብቻ መሙላት ይኖርባቸዋል፤ ማንኛውም ስርዝ ድልዝ፣ ማህተም ያልተደረገበት የቀረበ ዋጋ፣ በሆስፒታሉ ዋጋ መሙያ ቅጽ ያልተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል፡፡

11. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- በአራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ከዮሐንስ ቤ/ክ 500 ሜትር አለፍ ብሎ እንገኛለን፡፡ በተጨማሪ ማብራሪያ

አድራሻ፡-

ከፒያሳ ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ከዮሐንስ ቤ/ከ 500 ሜትር አለፍ ብሎ እንገኛለን።

ስተጨማሪ ማብራሪያ፦

በስልክ ቁጥር 0111112056 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል

Save Tender