በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙርግልጽ ጨረታ የጽዳት ዕቃዎች፣ እላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች እና የደንብ ልብስ ስፌት በግልፅ ጨረታ አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙርግልጽ ጨረታ የጽዳት ዕቃዎች፣ እላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች እና የደንብ ልብስ ስፌት በግልፅ ጨረታ አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታ መወዳደር የሚችሉ አቅራቢዎች
1. በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
3. የ2018 ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና የነቢዎች ጽ/ቤት ጨረታ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ
4. የአቅራብነት የተመዘገቡና /ከአቅራብነት ያልተወገዱ
5. ከ2,000,000.00 ብር በላይ ለሆነ የግዥ ዋጋ ቫት የተመዘገበ
6. የገቢዎች ቢሮ የፈቀደውን ደረሰኝ ስያመጣ ብቻ ከፍያ የሚፈጸምለት መሆኑን አውቆ ማዘጋጀት የሚችል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት CPO የባንክ ዋስትና በአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ባንክ ማስያዝ ያለባቸው ገንዘብ መጠን በየሎቱ፡-
|
ሎት |
የዕቃ / የአገልግሎት ዓይነት |
ከጠቅላላ ግዥ በመቶኛ |
የብር መጠን |
|
1 |
አላቂ ቢሮ ዕቃዎች |
1 |
19,766.00 |
|
2 |
ለጽዳት ዕቃዎች |
1 |
24,240.00 |
|
3 |
የደንብ ልብስ |
1 |
15,000.00 |
|
4 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
1 |
5,000.00 |
8. የጨረታው አሸናፊዎች አሸናፊ መሆናቸው እንደ ተገለጸ የውል ማስከበሪያ የዕቃው ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መግባት እና በ15 ቀን ዉስጥ ዕቃውን በራሳቸው ወጪ በአ /ከ ከ/ከወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ከፍል ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
9. የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መግዘት ይችላሉ፡
10. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት እና እዛዉ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውን ከላይ ከ1 - 4 የተጠቀሱትን ሰነዶች ኮፒ እና CPO በአንድ ላይ ማሸግ፣ እንድሁም የማይከፈት የፋይናንሻል ኮፒ ለብቻ ማሸግ እና የቴከኒካል ምርመራ የሚያገለግሉ ፎቶ ስፔስፍኬሽን... የመሳሰሉትን ሰነዶች ደግሞ ለብቻ በማሸግ በሁሉም ሰነዶች ላይ ኦሪጅናል፤ ኮፒ፤ ናሙና ብሎ በመጻፍ በሁሉም ፖስታዎች ላይ ሙሉ አድራሻ በትከከል በመሙላት ሁሉንም ሰነዶች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
13. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መሞላት ያለባቸዉ ከፍሎች በሙሉ መሞላት አለባቸው፤ በተጫራቾች መሞላት ያለበት ከፍል ያልሞላ እና የጨረታ ሰነዱ እና የዋጋ ማቅረብያው ሳይለወጥና ሳይቀነስ በሙሉ የማይመልስ አቅራቢ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
14. በሥራ ከህሎት ጽ/ቤት የተደራጃቹ በራሳቹ በምታመርቱ ምርት ላይ ልዩ አስተያየት ስለምደረግና የጨረታ ሰነዱንም ያለ ግዥ ስለሚትወስዱ አምራች መሆናቹን ካደራጃቹ አካል የድጋፍ ደብዳቤ እንዲሁም አምራች መሆናቸውን የሚገልፅ መረጃ አብሮ ማቅረብ አለባቹ፡፡
15. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያውኑ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።፡ 11ኛው ቀን ሥራ የለለበት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታን ከመክፈት አያግደውም፣
16. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ 2 ቀን በፊት ለሁሉም ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ መቻል አለባቸዉ፤ የናሙና መቀቢያ ቅፅ በ2 ኮፒ አዘጋጅቶ የድርጅቱ ማህተም በማድረግ አብሮ ማቅረብ መቻል አለባቸው፡፡
17. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ VAT ጨምሮ ያለ ስርዝ ድልዝ በትከከል መሞላት አለበት፡፡
18. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው ከሆነ ተቀባይነት የለውም፣፣
19. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
20. ዘግይቶ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
21. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 4 አስተዳደር ሰፈረ ሰላም ትምህርት ቤት ፌትስፌት የፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-279-3338
የአዲስ ከተማ ክፍስ ከተማ የወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት
