Tender Detail

Tender Details

  • Company South Water Works Construction Enterprise(SWWCE) (ደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት)
  • Address ደቡብ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline26 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security20%
  • opening date2025-12-26 00:00:00
  • Categories Machinery , Vehicle

የደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ያገለገሉ የተለያዩ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች፣ ተጫራቾች በተገኙበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

South Water Works Construction Enterprise(SWWCE) (ደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት)


 

ለአራተኛ ዙር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር NCB-01/2018

 

የደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ያገለገሉ የተለያዩ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች፣ ተጫራቾች በተገኙበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እና በተጠቀሱ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙትን ለሽያጭ የተዘጋጁ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ የጨረታ ሰነድ በመግዛት መመልከት ይችላል፡፡

 

ሎት

የዕቃዎች ዝርዝር

01

ያገለገሉ የተለያዩ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች

 

  1. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ከታች በተጠቀሰው የድርጅቱ ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ፤ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ /Bank slip/ ይዞ በመቅረብ ክብሎክ ቁጥር 9 ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታው ሠነድ የሚሸጥበት ጊዜ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ የሥራ ቀናት በስራ ሰዓት ይሆናል፡፡
  3. ሠነዱን ለመግዛት የሚመጡ ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው ንብረቶችን ማየት የሚችሉት ሠነዱን ከገዙ በኋላ የዙትን ሠነድ ኦርጅናሉንና ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያቸውን በማሳየት ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ያልያዘ ወደ ጨረታ አዳራሽ መግባት አይችልም፡፡
  5. የጨረታው ሰነድ 1 /አንድ/ ኦሪጅናል እና 2 ሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። የጨረታው ዋጋ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫትን/ ያካተተ ይሆናል እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 20% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሠነዱ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በ15ኛው ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 መግባት ይኖርበታል፡፡
  6. በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው የሠራተኞች መሰብሰቢያ አዳራሽ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የተለየ ሁኔታ ካለ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ዝርዝር ዕቃዎች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ / CPO/ ለ60 /ስልሣ/ ቀን የሚቆይ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ከተዘረዘሩት ዕቃዎች በሙሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ምንም ዓይነት የጨረታ ሠነድ ሽያጭ አይከናወንም።
  9. ጨረታውን ያሸነፈው አካል ክፍያውን የሚፈጽመው ለዚሁ ጉዳይ በተከፈተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የድርጅቱ ሂሳብ ቁጥር (1000013538542 ደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ኤች አይ ቪ) በማስገባት የባንክ ደረሰኝ (Bank slip) በማቅረብ ይሆናል።
  10. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ ከላይ በተጠቀሰው በድርጅቱ ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለበት። ገንዘቡን ገቢ አድርጎ ንብረቱን በ10 (አሥር) ቀናት ውስጥ ያላነሳ ተጫራች ያስያዘው ሲፒኦ /CPO/ 20% ውርስ ተደርጎ መግዛት ለሚፈልግ ለሌላ ተጫራች በአሸናፊው ዋጋ ድርጅቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመሸጥ ይችላል፡፡

 

ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት

 

Save Tender