በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ የቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የቢሮ ግንባታ ለማስገንባት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ የቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የቢሮ ግንባታ ለማስገንባት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ጨረታውን መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል
- የታደሰ የግንባታ ስራ ፈቃድ ያለው፣ በጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት ደረጃ-5/GC-5/ እና ከዚያ በላይ/በግንባታ ስራ ተቋራጭነት ደረጃ-5/BC-5/ እና ከዚያ በላይ የሆነ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የሆኑ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያላቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፊያ ማዘዣ/CPO/200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ለሰሜን ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት በማለት አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን ከሰሜን ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ፍይናንሻልና ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዱን ለየብቻ በማሸግ እና በጥቅል በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች እያንዳነዱን ፖስታ በሰም ታሽጎ ማህተም በመምታትና ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም ኦርጅናል እና ኮፒ የሚል ፅሁፍ በግልጽ ማስፈር አለባቸው።
- ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ በ21ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበትም ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ የቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት
