ላፓልማ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሂሳብ አጣሪ ኮሚቴው በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት አዲስ አበባ ቃሊቲ አምባሰል መጋዘን ግቢ ውስጥ የሚገኙ የፋብሪካው ማሽነሪዎች፣ ተሽከርካሪ እና ልዩ ልዩ ብረታ ብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ላፓልማ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የማሽኖችና ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሰንዳፋ ከተማ በንጋት ኮርፖሬትና ሌሎች ባለአክስዮኖች የተቋቋመው ላፓልማ ኃ.የተ. የግል ማኅበር የተባለው እና ለቢራና ለስላሳ ማጣሪያ ለማምረትና ለመሸጥ ተቋቁሞ የነበረው የንግድ ማኅበር በባለአክሲዮኖች ስምምነት እንዲፈርስ እና እንዲዘጋ መወሰናቸውን ተከትሎ ይህን የመዝጋት ኃላፊነት የሚወጣ የሂሳብ አጣሪ ኮሚቴ ሹመዋል፡፡ የሂሳብ አጣሪ ኮሚቴው በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት አዲስ አበባ ቃሊቲ አምባሰል መጋዘን ግቢ ውስጥ የሚገኙ የፋብሪካው ማሽነሪዎች፣ ተሽከርካሪ እና ልዩ ልዩ ብረታ ብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- ከባለአክሲዮኖች እና ከሂሳብ አጣሪ ኮሚቴ ሠራተኞች ውጭ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የንብረቶችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚከናወነው በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አምባሰል ሕንፃ በሚገኘው አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 ንጋት ኮርፖሬት አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ወይም ባሕር ዳር ንጋት ኮርፖሬት ዋናው መ/ቤት ቀበሌ 16 አምባሰል ሕንፃ ጀርባ ንጋት ኮርፖሬት በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 03 ሲሆን ይህ ማስታወቂያ ከተገለጸበት ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍሎ መውሰድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን እቃ መነሻ ዋጋ መሰረት በማድረግ የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ. ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በላፓልማ ኃ.የተ.የግ. ማህበር ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ንብረት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ (በማስታወቂያ) ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አምባሰል ሕንጻ በሚገኘው ንጋት ኮርፖሬት አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አምባሰል ሕንጻ አንደኛ ፎቅ በሚገኘው ንጋት ኮርፖሬት አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 የሚከፈት ሲሆን የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀው ቦታ ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አምስተኛው ተከታታይ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ንብረቶች ባሉበት ቦታ በመሄድ ማየት ይችላሉ። እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተፃፈውን በአካል ካለው ጋር በማረጋገጥ ልዩነት ካለ ጨረታው ከመዘጋቱ 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በፊት ለድርጅቱ ማሳወቅ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በተናጠል እና በጥቅል (በሎት) በሽያጭ ዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ መሰረት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በታሸገ ፖስታቸው ላይ ስም፣ ፊርማና ስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0933 634 958 ወይም 0933 633 818 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ኮሚቴው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ላፓልማ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
