በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአለታ ወንዶ ከተማ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አላቂ የቢሮ የጽሕፈት መሳሪያዎችን በጨረታ ዋጋ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአለታ ወንዶ ከተማ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
የአላቂ የቢሮ የጽ/መሳሪያ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
1. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአለታ ወንዶ ከተማ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አላቂ የቢሮ የጽሕፈት መሳሪያዎችን በጨረታ ዋጋ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- አግባብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና የዘመኑን ወይም 2018 ዓ.ም ግብር የገበሩበት ማረጋገጫ ያለው/ያላት አሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል። የ2018 ዓ.ም የግብር ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፡፡ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል። ጊዜው ያላለፈበት በአቅራቢነት በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግስት መ/ቤት የተሠጠ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 30,000 ከታወቀ ባንክ /CPO/ ማስያዝ የሚችል። የውል አፈፃፀም ዋስትና ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 10% በጥሬ ወይም ከታወቀ ባንክ የተሰጠ /CPO/ ማስያዝ የሚችል፡፡
- ማንኛውንም ወጪዎች ማለትም የጉምሩክ የትራንስፖርት የባንክ እና የሌሎች አገልግሎት ወጪዎችን በራሱ ሸፍኖ ዕቃውን ማሰረከብ የሚችል፡- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ያቀረቡት ናሙና ወዲያው ተመላሽ ይደረጋል። ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ለአ/ወ/ከ/ዝ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል እና ሰነዱን ከአ/ወ/ከ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነዱ ላይ የአንዱን ዋጋ ብቻ በመሙላት ቴክኒካል ዶክመንት እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እንዲሁም ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒው ለየብቻ በማድረግ በአንድ ፖስታ አሽጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአ/ወ/ከ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሳጥን በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒና ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አንደ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ሌላው ተጫራች ተንተርሶ መጫረት አይችልም፡፡
- የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ መያያዝ አለበት።
- ጨረታው መክፈቻ በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ 0462240152 እና 0462240627 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሱ፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአለታ ወንዶ ከተማ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
