በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ከነከማደሪያ (የውስጥ ፕላስቲክ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ
የጨረታ ማስታወቂያ
ዘርፉ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ከነከማደሪያ (የውስጥ ፕላስቲክ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘርፉ ለ2017/2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የፋይናኦሻል ሰነዳቸዉን ለብቻ በፖስታ በማሸግና የፋይናንሻል ሰነድ መሆኑን በመግለጽ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከሕዳር 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00-6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከሰአት ከ7፡30-11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡30 ሰዓት ድረስ ግዥ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። (አድራሻው ከስር ተገልጿል።)
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4:30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ ለተጠቀሰው፡- የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ከነከማደሪያ (የውስጥ ላስቲክ) ግዥ ብር 50,000.00 (ሐምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው። ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም። የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ዋጋ ፋይናንሻል፤ ቴክኒካል ፤ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ከሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ከዋና የመወዳደሪያ ሀሳብ (አሪጅናል) በተጨማሪ የሚፈለጉ ኮፒዎች ብዛት 1 (አንድ)
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን 10 ፐርሰንት /አስር ፐርሰንት በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ስም አሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል።
- ዘርፉ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 011 4552358
አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ
