Tender Detail

Tender Details

  • Company የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት
  • Address መማራቶን ሕንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ፎቅ የመንግስት ግዥ ቡድን ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118107894
  • Website
  • Deadline19 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-19 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Office Supplies And Services , Electronics Materials

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለ 2018 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቋሚ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት 001/2018

 

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የግዥ ቡድን 2018 የቋሚ እቃዎች ግዥዎች ጨረታ

  • ሎት 1- የቋሚ እቃ ግዥዎች ጨረታ

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትጫረቱ ይጋብዛሉ፤

  1. ተጫራቾች በሚሳተፉበት የግዥ አይነት በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀትና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው የገቢ ግብር ባለስልጣን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) የካ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሎቱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፣
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ፋይናንሺያል ዶክመንት እና ቴክኒካል ሰነድ ለየብቻ ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በመግለጽ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  7. የጨረታ ሰነድ እስከ 10 ቀን ብቻ ተሸጦ የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና ቫትን ያካተተ መሆኑና አለመሆኑ ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  9. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  10.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11.  የሚወገዱ ንብረቶችን ለማየት የሚፈልግ ተጫራች በየካ/ክ/ከተማ (ቤዝመንት) ግራውንድ ውስጥ ማየት ይችላል፡፡

 

አድራሻ፡- መገናኛ ማራቶን ሕንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ፎቅ የመንግስት ግዥ ቡድን

 

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት

 

Save Tender