Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢስት ዌስት ኢትዮ ትራንስፖርት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: 251114392038
  • Website
  • Deadline16 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security10%
  • opening date2025-12-16 00:00:00
  • Categories Vehicle

ኢስት ዌስት ኢትዮ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግል ማህበር የድርጅቱ ንብረት የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ ኬንወርዝ ጎታች፤ ሬኖ ጎታች እና ሎርሲ ተሳቢ ቦቴዎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ኢስት ዌስት ኢትዮ ትራንስፖርት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢዌኢት/ግጨ/01/2018

ኢስት ዌስት ኢትዮ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግል ማህበር የድርጅቱ ንብረት የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ ኬንወርዝ ጎታች፤ ሬኖ ጎታች እና ሎርሲ ተሳቢ ቦቴዎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ሁኔታዎች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በሪፖርተርና በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ህዳር 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ በሚገኘው ከድርጅቱ ዋና መ/ቤት ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ከፍለው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:30 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዕቃዎችን ቃሊቲ ከጣና ኢንጂነሪንግ ወረድ ብሎ አዲስ በሚሰራው ስታዲየም ፊት ለፊት በሚገኘዉ የድርጅቱ ተሽከርካሪ ማቆሚያ ተርሚናል-2 ግቢ ውስጥ በመምጣት መመልከት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች በሚጫረቱበት ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ አስር በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (Bid Bond) በኢስት ዌስት ኢትዮ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግል ማህበር (EAST- WEST ETHIO TARANSPORT PLC) ስም ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በማሸግ የጨረታ ቁጥሩን በመግለጽ እስከ ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዒ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ብቻ በዋናው መ/ቤት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፣ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላስያዙ ተጫራቾች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋሉ፡፡

4. ጨረታው ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት የሰራተኞች ክበብ ይከፈታል፡፡

5. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር +251114392038፤ +251911817662 እና +251911207223 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ኢስት ዌስት ኢትዮ ትራንስፖርት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

Save Tender