Tender Detail

Tender Details


በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን የመ/ማ/ም/ጠ/ፍ/ቤት በ2018 በጀት አመት የሚከተሉትን አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መገዛት ይፈልጋል፡፡

በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን የመ/ማ/ም/ወ/ፍ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን የመ/ማ/ም/ጠ/ፍ/ቤት በ2018 በጀት አመት የሚከተሉትን አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መገዛት ይፈልጋል፡፡

1. ሎት 1 አላቂ የጽ/ህፈት መሳሪያ ሌሎች አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች

2. ሎት 2 ደንብ ልብስ /ብትን ጨርቅ ጫማ፣ የተዘጋጀ ልብሶችንና የመሳሰሉት/ ይጨምራል

3. ሎት 3 የፕላንት ማሽነሪ መሳሪያና ተዛማጅ እቃዎች/ ኮምፒዩተርና ላብቶፕ ከነአክሰሰሪው የመሳሰሉት/

4. ሎት 4 ህትመት /ፋይል ፎልደር፣1-9 ልብስ ቁጥር ፣ የችሎት ወረቀት ቲተር/

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣

4. የግዢው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤

6. የሚገዙት እቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፤

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 50 ብር በመከፈል በገንዘብ ያዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፤

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዣዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ ሞልተው እንዲያቀርቡ አይገደዱም

10.የመጫረቻ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ማ/ም/ወ/ፍ/ቤት በግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ25/03/2018 ዓ/ም እስከ 09/04/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

11.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋ/ን/አ ስ/ደ/የስራ ሂደት በቢሮ ቁጥር 5 በ09/04/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡15 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣

12.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13.ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን አሁድና ቅዳሜ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

14.ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የሚሙሉት የነጠላ ዋጋ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ፡፡

15. አሸናፊው ድርጅት/ግለስብ /አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ወደያውኑ ውል በመያዝ ንብረቶቹን ገዝቶ ንብረት ከፍል ማስገባት አለበት፤

16.በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0116220148/ 0921139915 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን የመ/ማ/ም/ወ/ፍ/ቤት

Save Tender