ዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ በ2018/9 ምርት ዘመን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ለሚገኙ ለአራት ገጠር ወረዳዎች እና ለሶስት ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ለማረቆ ልዩ ወረዳ የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት የሚያከናውኑ ህጋዊ የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ከቡታጅራ ማዕከላዊ መጋዘን ወደ ገጠር ወረዳና ከተማ አስተዳደር ማሰራጫ ጣቢያዎች ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
ዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላ.የተወሰነ
የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዋገዩ 001/2018
ዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ በ2018/9 ምርት ዘመን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ለሚገኙ ለአራት ገጠር ወረዳዎች እና ለሶስት ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ለማረቆ ልዩ ወረዳ የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት የሚያከናውኑ ህጋዊ የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ከቡታጅራ ማዕከላዊ መጋዘን ወደ ገጠር ወረዳና ከተማ አስተዳደር ማሰራጫ ጣቢያዎች ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት በጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ግዴታዎች ማሟላት አለባቸው፡፡
- በደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸው ማረጋገጫ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 500 በመክፈል የጨረታው ሰነድ ከዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የዩኒየኑ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 300,000 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ /ሲፒኦ/ CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታውን በወጣ 15ኛ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በቡታጅራ ከተማ በዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱን ህጎች ማከበር የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልከ ቁጥር 0461151110/ 0916272305 /0926854527 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላ.የተወሰነ
