የፍርድ ባለ መብት አነስ ኢብራሂም እና የፍርድ ባለ እዳ አዲስአለም እድገቱ መካከል ያለውን የአፈጻጸም ከርክር በተመለከተ :-
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የፍርድ ባለ መብት አነስ ኢብራሂም እና የፍርድ ባለ እዳ አዲስአለም እድገቱ መካከል ያለውን የአፈጻጸም ከርክር በተመለከተ ከባለ እዳው አቶ አየለ ጌታቸው ላይ እዳ ስለሚፈለግ የፍርድ ባለ እዳው አቶ አየለ ጌታቸው ንብረት የሆነው ካርታ ቁጥር 1- 250-1232-2005 የሆነ መጋዘን ንብረትነቱ የፍርድ ባለእዳ የሆነ ጭሮ ከተማ አስተዳደርቡርቃ ጭሮ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ ስፋቱ 433.5 ካ.ሜትር የሆነ እና አዋሳኞቹ በምስራቅ ይሱፍ መሐመድ በምእራብ ዶ/ር ወርቁ ከታብ፣ በደቡብ ሁሴን አመዴ ጋር የሚዋሰን ለ30 ቀናት ማለትም ከቀን 11/03/2018 3፡00 ሰአት ጀምሮ እስከ ቀን 11/04/2018 6 ሰአት ድረስ ጨረታው ቤቱ በሚገኝበት ቦታ ተለጥፎ በአየር ላይከዋለ በኋላ መጋዘኑ በሚገኝበት ከላይ በተገለጸው ቦታ በቀን 12/04/2018 ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ በጨረታ መነሻ ብር 4,749.482.35 (አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ሁለት ብር ከ35 ሳን.) ለመሽጥ የምእራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጨረታ ስላወጣ በዚህ ጨረታ ተወዳድራችሁ መጋዘኑን መግዛት የምትፈልጉ ሰዎች በዚሁ በተባለው እለት ይህ መጋዘን የሚገኝበት ቦታ በአካል ተገኝታችሁ በዚህ በተባለው ሰአት ውስጥ ተመዝግባችሁ ተወዳድራችሁ ቤቱን እንድትገዙ እናሳውቃለን፡፡
የምእራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
