የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት ለኮሌጁ ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2018
የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት ለኮሌጁ ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ፡-
1. ብረታ ብረቶችና የብረታ ብረት ስራ መሳሪያዎች፣
2. የእንስሳት ጤና ሳይንስ ሥልጠና መሣሪያዎች፣
3. አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የጽ/መሣሪያዎች፣
4. የአይሲቲ ስልጠና ቁሳቁሶች፣
5. የሠራተኞች ደንብ ልብስና ጫማዎች፣
6. የቢሮ ፈርኒቸር፣
7. Garment ሥልጠና መሣሪያዎች፣
8. Animal since ሥልጠና መሣሪያዎች፣
9. plant since ሥልጠና መሣሪያዎች፤
10, BEI/ የኤሌክትሪክ እንስታሌሽን ሥልጠና መሣሪያዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የስራ ፈቃድና የዘመኑን የስራ ግብር አጠናቀው የከፈሉበት ማስረጃ፣ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ ተጨማሪ የእሴት ታከስ ተመዝጋቢ እና የንግድ መለያ ቁጥር/Tin number/ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር /300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ከ/መ/ ሸካ ዞን ማሻ ከተማ ከሚገኘው ከማሻ ኮ/ኢን/ኮሌጅ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለት/ት መሳሪያዎች ብር 5000.00/አምስት ሺህ ብር/፣ ለደንብ ልብስና ጫማዎች ብር 2000/ሁለት ሺህ ብር/ ፣ ለአላቂ የቢሮ ዕቃዎችና ጽ/መሳሪያዎች 2000/ሁለት ሺህ ብር /እና ለፈርኒቸር 2000.00/ ሁለት ሺህ ብር/ CPO ከታወቀ ባንከ አስይዘው ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የተሟላ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የመንግስት የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው 16ኛው ቀን የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል።
6. 16ኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል።
7. የጨረታ አሸናፊ ከተለየ በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው 10% በCPO ወይም በጥሬ በማስያዝ ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታ አሸናፊ የሆነው አቅራቢ በራሱ ወጪ ዕቃዎችን አጓጉዞ እስከ ኮሌጁ ግቢ በማቅረብ ማስረከብ አለበት
9. የፈርኒቸር፣ የሰራተኞች የደንብ ልብስ ጨርቅ ናሙናዎችን /በፎቶ/ መቅረብ ይኖርባቸዋል።
ኮሌጁ የተሻሉ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 0910095932/0917164056 መደወል ይችላሉ።
የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
