አድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን ለ2018/19 የምርት ዘመን የሚውል ዳፕ እና ዩሪያ የአፈርማዳበሪያ በጉራጌ ዞን ላሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለማሠራጨት ህጋዊ የሆኑ ሀገር ውስጥ ደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
አድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን
የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ ለሁለተኛ ዙር የወጣ
ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አድገዩ/002/2018 ዓ.ም
አድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን ለ2018/19 የምርት ዘመን የሚውል ዳፕ እና ዩሪያ የአፈርማዳበሪያ በጉራጌ ዞን ላሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለማሠራጨት ህጋዊ የሆኑ ሀገር ውስጥ ደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች ማሟሳት የሚችል በዘርፉ የተሰማራ ማንኛውም የሀገር ውስጥ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ድርጅት በጨረታው መሳተፍ የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፦
1. በደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸው ማረጋገጫ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
2. በጨረታው ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመከፈል የጨረታውን ሰነድ ከአድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዩኒየኑ ፅ/ቤት ድረስ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 350,000 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ ሲፒኦ /CPO/ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከዩኒየኑ ሂሳብ ክፍል የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 8:30 በዩኒየኑ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱን ህጎች ማከበር የሚችል መሆን አለበት፡፡
6. የኑያኑ በትራንስፖርት ጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
7. ተጫራች ድርጅት ከዚህ በፊት በአድማስ ኃላ/የተ/የገ/ኅ/ስራ ዩኒየን የወጡ ጨረታዎችን ካሸነፈ በኋላ ግዴታውን በአግባቡ የተወጣ መሆን አለበት፣
8. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር፡-0113301519/0936780943/0912 775381 በመጠቀም ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
ጉራጌ ዞን
ወልቂጤ
የአድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን
