Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
  • Address ባህርዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-222-11-00
  • Website
  • Deadline17 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityየእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 500,000.00 /ከአምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ
  • opening date2025-12-17 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Mechanical Work and Materials

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ አይቬኮ የውሃ ቦቴ አጠቃላይ የቦዲ፣ የመካኒካልና የኤሌክትሪካል ሲስተም የጥገና አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)


 

ድጋሜ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ገመኮኤ 03/2018

 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ አይቬኮ የውሃ ቦቴ አጠቃላይ የቦዲ፣ የመካኒካልና የኤሌክትሪካል ሲስተም የጥገና አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው፣
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በኤጀንሲው ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ደረሰኝ በማስቆረጥ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው፣ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 500,000.00 /ከአምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ማስገባት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት ቀን 23/03/02/2018 ጀምሮ እስከ ቀን 07/04/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትና ሌሎች ታክስ፣ የትራንስፖርት ዋጋ እንዲሁም የመጫኛ እና ማውረጃ ወጪን ጨምሮ መሆን አለበት።
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ወይም አዳራሽ በ08/04/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር 08:30 ወይም ኤጀንሲው አዳራሽ ይከፈታል።
  10. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  11. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር-08 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-222-1115/058-320-7769 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  13. ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፉ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።

 

ባህርዳር ፖ.ሣ.ቁ 382

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

 

Save Tender