Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa city Urban Beautification and Green Development Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ)
  • Address የካ/ክ/ከተማ ቀበና አካባቢ ኬንያ ኢንባሲ ፊት ለፊት 2ኛ ፎቅ ግዥ ዳይሬክቶሬት ክፍል ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115 58 11 79
  • Website
  • Deadline11 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Security10%
  • opening date2025-12-11 00:00:00
  • Categories Vehicle

በዚህ መሰረት፦ የከ/ው/አረ/ል/ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት በሎት (1) የውሃ ማጠጫ ቦቴ መኪና እና በሎት (2) የቀላል መኪና የጥገና አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Addis Ababa city Urban Beautification and Green Development Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ)


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር የከ/ው/አ/ስ/ቢሮ/ግ/ጨ/02/2018

በዚህ መሰረት፦ የከ/ው/አረ/ል/ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት በሎት (1) የውሃ ማጠጫ ቦቴ መኪና እና በሎት (2) የቀላል መኪና የጥገና አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተለውን ማሟላት አለባቸው፡፡

  • በዘርፉ የተሰማሩ እና የዘመኑን የግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (Tin No) ፤ ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑበት ሰርተፊኬት፤ በአቅራቢነት የተመዘገበና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ10 የስራ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን አድራሻችን የካ/ከ/ከተማ ቀበና አካባቢ ኬንያ ኤንባሲ ፊት ለፊት 2ኛ ፎቅ ግዥ ዳይሬከቶሬት ከፍል እንገኛለን፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን ለእያንዳንዱ ሎት ቴከኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጂናል እና አንድ ኮፒ፣ ፋይናሻል አንድ ኦሪጂናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በወጣ እስከ ከኛው የስራ ቀናት ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥኖች ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት(1) ብር 50,000፣ለሎት (2) ብር 50,000 በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  • ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በዘኛው የስራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ግዥ ዳይሬከቶሬት ክፍል ይከፈታል፡፡
  • ጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊዎች ተለይቶ ውል እስኪፈፅሙ እንደተያዘ ይቆያል፡፡
  • ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በቢሮው ስም የተዘጋጀውን በማስያዝ በሰባት ቀን ውስጥ ውል ተዋውሎ ወደ ስራ መግባት ይኖርባችኋል፡፡
  • የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል፡፡
  • ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  • ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተውና በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን (VAT) ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  • ተጫራቾች ጨረታ ለማስገባት በምትመጡበት ጊዜ ቴክኒካል ኮፒና ኦርጂናል፣ ፋይናንሻል ኮፒና ኦርጂናል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0115 58 11 79 ደውለው ይጠይቁ፡፡
  • ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ሰነዱን ለመግዛት በምትመጡበት ጊዜ በመስኩ የተሰማራችሁበትን ንግድ ፍቃድ ኮፒ መያዝ እንዳትረሱ፡፡
  • ዝርዝር የግዥ አገልግሎቶችን ለማየት በ telegram ገፃችን https://t.me/ addisabebagreenarea እና
  • facebook ገጻችን https://www.facebook.com/aaurbanbeutification ይመልከቱ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ

Save Tender