የአማራ ብሔ/ክ/መ/የሰ/ሸዋ/ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ግ/ን/አሰ/ቡድን ለመ/ጌ/ም ወ/ትም/ጽ/ቤት በ010 ቀበሌ በመደበኛ በጀት እናቴ ሜዳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 1 ብሎክ ባለ 4 መማሪያ ክፍል ግንባታ የእጅ ዋጋ ብቻ እና በ014 ቀበሌ ባጎድ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የሴቶች መፀዳጃ ቤት ግንባታ 1 ብሎክ ባለ 4 ቀዳዳ እና የወንዶች መፀዳጃ ቤት ግንባታ 1 ብሎክ ባለ 4 ቀዳዳ እንዲሁም የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ 1 ብሎክ እና የቆሻሻ ማቃጠያ ከነሙሉ አቅርቦት በዋንዋሽ በጀት ከላይ ከላይ የተጠቀሱትን ግንባታዎች ከደረጃ 6 እና በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸውን አጫርቶ ማስገንባት ይፈልጋል።
የአማራ ብሔ/ክ/መ/የሰ/ሸዋ/ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2018
የአማራ ብሔ/ክ/መ/የሰ/ሸዋ/ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ግ/ን/አሰ/ቡድን ለመ/ጌ/ም ወ/ትም/ጽ/ቤት በ010 ቀበሌ በመደበኛ በጀት እናቴ ሜዳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 1 ብሎክ ባለ 4 መማሪያ ክፍል ግንባታ የእጅ ዋጋ ብቻ እና በ014 ቀበሌ ባጎድ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የሴቶች መፀዳጃ ቤት ግንባታ 1 ብሎክ ባለ 4 ቀዳዳ እና የወንዶች መፀዳጃ ቤት ግንባታ 1 ብሎክ ባለ 4 ቀዳዳ እንዲሁም የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ 1 ብሎክ እና የቆሻሻ ማቃጠያ ከነሙሉ አቅርቦት በዋንዋሽ በጀት ከላይ ከላይ የተጠቀሱትን ግንባታዎች ከደረጃ 6 እና በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸውን አጫርቶ ማስገንባት ይፈልጋል ስለዚህ
- ሎት 1 እናቴ ሜዳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 1 ብሎክ ባለ 4 መማሪያ ክፍል የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/ ማሲያዝ የሚችል
- ሎት 2 የሴቶች መፀዳጃ ቤት፣ የወንዶች መፀዳጃ ቤት፣ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ እና የቆሻሻ ማቃጠያ የጨረታ ማስከበሪያ 60,000 /ስልሳ ሺህ ብር/ በማሲያዝ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው ኮንትራክተር መሳተፍ ይችላል፡፡
ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ከ23/3/2018 ዓ.ም እሰከ 14/4/2018 ዓ.ም ለ21 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ22 ኛው ቀን በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- በጨረታው የሚሣተፍ በዘመኑ የታደሠ የንግድ ስራ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር የቫት ተመዝጋቢ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የብቃት ማረጋገጫ መረጃውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ላይ የጨረታ መዝጊያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ራሣቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የሞሉበትን የጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙበትንም ደረሠኝ ከሆነ ፎቶ ኮፒ አድርገው ማቅረብ አለባቸው CPO ከሆነ ዋናውን ማቅረብ አለባቸው።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ያንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል።
- መ/ቤቱ ፋይናሻል እና ቴክኒካል ግምገማ ሲያደርግ ኦርጅናል ዶክሜንቶችን በአስፈላጊ ቀናት ውስጥ ኦርጅናል ዶክሜንት ከጠየቀ ተጫራቾች በአስቸኳይ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ጥሪ ተደርጎለት ለማቅረብ ፍቃደኛ ያልሆነ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል።
- በፖስታው ላይና እንዲሁም በጨረታ ዋጋ መሙሊያ የጨረታ ሠነድ ላይ የተጫራቾች ስምና ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል፡፡
- በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ተጫራቾች አሽናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽ/ቤታችን በመገኘት የውል ማስከበሪያ 10% በማሲያዝ ውል መፈፀም አለባቸው በተሠጠው የጊዜ ገደብ ውሰጥ ቀርበው ውል ካልፈፀሙ በግዥ መመሪያው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያውን ውርስ በማድረግ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅ መሠረት አሸናፊነቱ በተገለፀው በተከታታይ በ5 የስራ ቀን ውሰጥ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ።
- ለአሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሰያዙትን ብር ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል እንደተፈፀመ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም ተጫራቹ መሙላት አለበት፤ ሁሉንም ካልሞላ ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
- ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት የህዝብ በዓላት ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ድረስ በመምጣት ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በማይመለስ መግዛት የሚቻል ሲሆን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛትና መውሰድ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 011 6851161/0106 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገ/ቢሮ በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
