Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ ወማ ሁለገብ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር ኃላ/የተወሰነ
  • Address በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline09 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-09 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

በቀቤና ልዩ ወረዳ ወማ ሁለገብ መሰረታዊ የገበሬዎች ማኅበር ኃላ/የተወሰነ በተሰጠው ውክልና መሠረት የ2018/19 ምርት ዘመን የማዳበሪያ ጭነት አገልግሎት የሚሰጡትን ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማጫረት ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ ወማ ሁለገብ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር ኃላ/የተወሰነ


 

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ 0001/2018

 

በቀቤና ልዩ ወረዳ ወማ ሁለገብ መሰረታዊ የገበሬዎች ማኅበር ኃላ/የተወሰነ በተሰጠው ውክልና መሠረት የ2018/19 ምርት ዘመን የማዳበሪያ ጭነት አገልግሎት የሚሰጡትን ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማጫረት ይፈልጋል፡፡

ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱትን ግዴታዎች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

  1. አሸናፊው የትራንስፖርት ድርጅት በሚያጓጉዙ የአፈር ማዳበሪያ መጠን ሊከሰት ለሚችል ማንኛውም ጉዳይ የመድህን ዋስትና የመግዛትና የማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
  2. በማጓጓዝ ሂደት ወጪ ያደረገው የአፈር ማዳበሪያ ቢጠፋበት፣ ቢበላሽበትና፣ ቢጎድልበት ወዲያውኑ በሚተመነው ተመን መሰረት የመተካት ግዴታ አለበት፡፡
  3. አጓጓዥ ድርጅት የሚጭነውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት፣ መጠን እና ጥራት አጣርቶ ማስጫን አለበት፤ ተጭኖ የሄደው የአፈር ማዳበሪያ በጥራት ችግር ወይም በብልሽት ምክንያት ተረካቢ ወረዳ/ ጣቢያ አልረከብም ካለ ትራንስፖርተሩ ራሱ ወጪውን ተመላሽ ያደርጋል።
  4. ጭነቱን በሚገቡት ውል መሰረት በተወሰኑ የጊዜ ገደብ ውስጥ አጓጉዞ የመጨረስ ግዴታ አለበት፡፡
  5. ተረከቦ በሚገቡት ንብረት የተረከበ ንብረት ለማድረሳቸው ከተቀባይ ሕጋዊ ኅ/ሥራ ማኅበር ማህተም ያረፈበትና በተቀባይ ፊርማ የተረጋገጠ የዩኒየኑ ወጪ የተደረገለት ጣቢያ የአፈር ማዳበሪያ የገቢ ደረሰኝ ሰነድ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  6. ጠንካራ ብቁና አስተማማኝ መኪናዎች ማሰማራት ስራው ሳይቋረጥ በወቅቱ የማጓጓዝ እና የማጓጓዣ መኪናዎች ከነታርጋቸው በፈቃድ ሰጪ መንግሥት አካል የተረጋገጠ ማስረጃና የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይም የተሽከርካሪ ሊብሬ በባንክ ብድር የተያዘ ከሆነ ከአበዳሪው ባንክ ደብዳቤ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  7. ማንኛውም በጨረታ የሚሳተፍ ድርጅት አንድ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ የሚሰጠው ዋጋ እንደ አካባቢው የመንገድ አውታር ሁኔታ ለአንድ ኪ/ሜትር እንደ የማራገፍ ጣቢያ የርቀት ሁኔታ የተገናዘበ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ውጪ ግን የሚሰጥ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
  8. ማንኛውም ተጫራች በተቀመጠው ላይ ዋጋ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
  9. በአጎራባች ወረዳዎች ለሚገኙ ጣቢያዎች የተሰጠው ዋጋ ቅርበትና ርቀት ያላገናዘበ ከሆነ የቅርበት ዋጋ ለሩቅ የተሰጠውን ዋጋ መነሻ ማድረግ በኪሎ ሜትር ተሰልቶ ይስተካከላል፡፡
  10. በተራ ቁጥር 9 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በአጎራባች ወረዳዎች ላይ የተለያየ ትራንስፖርት ድርጅቶች አሸናፊ ቢሆኑና በአጎራባች ጣቢያዎች ላይ ርቀት ልዩነት ሳይኖራቸው የተሰጠ ዋጋ የተለያየ ከሆን ዝቅተኛ በሰጠው የትራንስፖርት ድርጅት ዋጋ መሰረት የሚስተካከል ይሆናል ፡፡
  11. የእያንዳንዱ የማራገፈያ ጣቢያ የመንገድ ሁኔታ በቦታው በመገኘት በአግባቡ አጥንተው ዋጋ መስጠት የተጫራቾቹ ኃላፊነት ነው። የጨረታ ዋጋ ከተሰጠ በኋላ የመንገዱን ሁኔታ በሚመለከት የሚቀርብ ማንኛውም ጥያቄ ተቀባይነት የለውም።
  12. በአንድ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ካጋጠመ አማራጭ ከተሰጠው ማዕከላዊ መጋዘን ከወደብ የተጓዘበት ሂሳብ እየተሰላ በመጨመርና በመቀነስ ክፍውን ልዩነት ተሰልቶ የማንሳት ግዴታ አለበት።
  13. ለአስተዳደር እንዲመችና ለጭነቱ ቀልጣፋና ወቅታዊ እንዲሆን አንድ ተጫራች ሁሉንም ወረዳዎች ቢያሸንፍም በቀን 1000 ኩንታል እና ከዚያ በላይ ማንሳት የሚችል መሆኑን በመረጃ ሲረጋገጥ ጨረታ ያወጣው አካል ከፍተኛ የአፈር ማዳበሪያ ተጠቃሚ ከሆኑት አንድ ወረዳ፣ መካከለኛ ተጠቃሚ አንድ ወረዳ፣ እንዲሁም አነስተኛ ተጠቃሚ ከሆኑት አንድ ወረዳ መርጦ ይሰጠዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች በልዩ ሁኔታ ካልተፈቀደ በስተቀር በዩኒየኑና በሚመለከተው አካል ተመርጦ ከተሰጠው 3 ወረዳ በላይ መሰረት አይችልም። ተመርጦ የተሰጠውም ወረዳ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በተሰጠው የትራንስፖርት ዋጋ መሰረት የመስራት ግዴታ አለበት፤ ነገር ግን ወረዳዎች የመምረጥ መብት አለው።
  14. በጨረታ የሚሳተፍ ማንኛውም ድርጅት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ሲፒኦ /CPO ብቻ ለወማ መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር ኃላፊነቱ የተወሰነ /Woma Peraumre Cooperative Itd/ በሚል ስም አሰርተው ማስያዝ ይጠበቅበቸዋል።
  15. ለሥራ አፈጻጸም ዋስትና አሸናፊ ድርጅቶች በሚያጓጓዙት የአፈር ማዳበሪያ መጠን ተሰልቶ ለማጓጓዝ ከሚፈለገው ገንዘብ በቅድሚያ 10% ሲፒኦ/ CPO ብቻ ወማ የገበሬዎች ኅ/ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ /Woma Peraumre Cooperative Ied/ በሚል ስም እሰርተው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
  16. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሰጥተው ባሸነፈባቸው ወረዳዎች ውል ከፈጸሙበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ የማይጀመር ከሆነ ያስያዘው ሲፒኦ /CPO አይመለስለትም፡፡
  17. ተጫራቹ ባሸነፈበት ቦታ ሥራውን ለመስራት ውል ከፈጸመ በኋላ በተለያየ ምክንያት ሥራውን ቢያቋረጥ ወይም ሥራውን ቢያጓትት ለሥራ አፈጻጸም ያስያዘውን 10% ሲፒኦ/CPO እና ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ/CPO አይመለስለትም፡፡
  18. ማንኛውም አሸናፊ ትራንስፖርት ድርጅት የአፈር ማዳበሪያ ከማዕከላዊ መጋዘን ጭኖ ከመነሳቱ በፊት ከዩኒየኖችና በየወረዳው ካሉ ሥራው ከሚመለከታቸው ኃላፊዎችንና ባለሙያዎች ጋራ መረጃ በመለዋወጥ ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ በየጊዜው ቀድመው የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡
  19. ማንኛውም አሸናፊ ድርጅት ወረዳዎች ከሚሰጡት የማራገፊያ ጣቢያዎች ቅደም ተከተል መሰረት በሁሉም ጣቢያዎች አጓጉዞ የማድረስ ግዴታ አለበት፡፡ በተሰጠው ቅደም ተከተል የሚያደርስ የትራንስፖርት ድርጅት ግን ለሚከሰተው ችግር ተጠያቂ ይሆናል፡፡
  20. ማንኛውም በጨረታው አሸናፊ የሆነ የትራንስፖርት ድርጅት በአሸነፈበት አካባቢ የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ ውክልና ከተሰጠው ወማ የገ/ኅ/ሥ/ዩኒየን ጋራ ወድያውኑ የውል ስምምነት በመፈጸም ስራውን ያከናውናል፡፡

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ ወማ ሁለገብ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር ኃላ/የተወሰነ

Save Tender