ከሁምቦ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በቁጥር ሁወጤና መ20/1196/08 በቀን 05/03/16 ዓ/ም ከሁምቦ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት በቁጥር ሁወት/40-5020/35 በቀን 05/03/18 ዓ/ም በተፃፈው ትዕዛዝ ደብዳቤ መሠረት በዋን ዋሽ ፕሮግራም በጀት ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ግንባታዎች በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።
የደ/ኢ/ክልላዊ መንግስት በወላይታ ዞን የሁምቦ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ከሁምቦ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በቁጥር ሁወጤና መ20/1196/08 በቀን 05/03/16 ዓ/ም ከሁምቦ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት በቁጥር ሁወት/40-5020/35 በቀን 05/03/18 ዓ/ም በተፃፈው ትዕዛዝ ደብዳቤ መሠረት በዋን ዋሽ ፕሮግራም በጀት ሎት-1 በአምፖ መስኖ ጤና ኬላ ባለ አራት ክፍል መጸዳጃ ቤት ግንባታ፣ በሾጮራ አበለ/በስሬ ጣውራታ፣ በፋንጎ ጌልጬጫ ቀበሌዎች የውሀ መስመር ዝርጋታና ደረቅ ቆሻሻ መጣያ ጉድጓድ ሥራ፤ በሾ/ፊሾና በቦሳ ዋንቼ ቀበሌ ጤና ኬላ የደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ ጉድጓድ ሥራ ሎት 2 ሾጮራ ጎላ 1ኛ ደ/ትም/ቤት የሴት ተማሪዎች ንጽህና መጠበቂያ /MHM/ ግንባታ፣ ሸጭራ ጎላ 2ኛ ደ/ትም/ቤት የሴት ተማሪዎች ባለ 4 ክፍል መጸዳጃ ቤት ግንባታ፣ ላይኛው ሁመቦ 2ኛ ደ/ት/ቤት የሴት ተማሪዎች ንጽህና መጠበቂያ /MHM/ ግንባታ፣ ላይኛው ሁመቦ 2ኛ ደ/ት/ቤት የሴት ተማሪዎች ባለ 4 ክፍል መፀዳጃ ቤት ግንባታ ለማሰራት ማቴሪያል አቅርበው በመ/ቤቱ በኩል በቀረበው ዲዛይንና ሥራ ዝርዘር መሠረት ባለሞያተኛን አጫርተን እንድናሠራላቸው ጠይቀውናል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
1. በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡ ደረጃቸው WWC/ GCC 7 እና ከዛ በላይ የሆኑና በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ተ.እ.ታ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የአቅራብነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት /EGP/ ማቅረብ የሚችል፣ ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል።
2. ከሚያገኘው ገቢ 3% መክፈል የሚችል።
3. ዝርዝር የጨረታው ሠነድ /ለዶክሜንቱ/ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ለወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ከሁምቦ ወ/ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት ከግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 07 ቀርበው መውሰድ ይችላል።
4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በቀጣይ ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ ሰንበት ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
5. ተጫራች በፖስታ ላይ ቀን ፣ ሙሉ ስም ከነአያት፣ አድራሻ ፣ ማህተም እና የፕሮጀክቱን ስም በትክክል ተደርጎበት በተለያየ ፖስታ በማሸግ ዋናውን፤ 2 ኮፒንና cpoን ጨምሮ አራቱን በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማድረግ ስርዝ ድልዝ የለሌበት ማቅረብ አለበት፡፡ ስርዝ ድልዝ ካለው ሠነዱ ተቀባይነት አይኖርም፡፡
6. በውድድር የወረደና የተጋነነ ዋጋ ከቀረበ በአዲሱ መመሪያና የመሐንድስ ግምት ተግባራዊ ይሆናል፡፡
7. የቀረበው ዋጋ በ3% ስለላ ከ3% የወረደና የተጋነነ ከሆነ ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
8. የጊዜ ሠሌዳ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
9. የጨረታ ሠነድ ከመሙላት በፊት የመስክ ጉብኝት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
10. የጨረታ ማስከበሪያ ከባንክ የተረጋገጠ CPO /ሲፕኦ/ የባንክ ጋራንቲና ቼክ ባለ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
11. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበት 10% ውል ማስከበሪያ CPO /ሲፕኦ/ ማስያዝ ይኖርበታል።
12. ከመ/ቤቱ ጋር በሚገባው ውል መሠረት ሥራውን በጥራት መሥራት የሚችል፡፡
13. በሌላው ዋጋ ላይ ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም ፡፡
14. ፖስታው ከተከፈተ በኋላ ራሰዎን ከጨረታው ማግለል አይቻልም።
15. ተጫራቾች ያልገባቸው ነገር ካለ ፖስታው ከመከፈቱ በፊት የማብራሪያ ጥያቄ ለመ/ቤቱ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡
16. ላለፉት 3 ዓመታት ከወረዳም ሆነ ከዞን ምንም ማስጠንቀቂያ ያልተሰጠውና መልካም ሥራ አፈጻጸም ያለው።
ከላይ ከተራ ቁጥር 1-16 የተዘረዘሩት መስፈርቶችን የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የሚትችሉ መሆናችሁን አየገለጽን መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 0938321152 /0916457554
የደ/ኢ/ክልላዊ መንግስት በወላይታ ዞን የሁምቦ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት
