የደ/ም/ኢት/ክ/መንግሥት የቤንች ሸኮ ዞን ሲዝ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ለአማካሪና የመንግሥት ተጠሪ መ/ቤት አገልግሎት የሚሆን የቢሮ ግንባታ ማከናወናቸውን በመግለጽ የቢሮዎቹን አጠቃላይ የበርና የመስኮት ግዥ እንዲፈጸምላቸው በጠየቁን መነሻ የሲዝ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተጠየቀውን የበርና መስኮቶች መግዛት ይፈልጋል።
የደ/ም/ኢት/ክ/መንግሥት የቤንች ሸኮ ዞን ሲዝ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ም/ኢት/ክ/መንግሥት የቤንች ሸኮ ዞን ሲዝ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ለአማካሪና የመንግሥት ተጠሪ መ/ቤት አገልግሎት የሚሆን የቢሮ ግንባታ ማከናወናቸውን በመግለጽ የቢሮዎቹን አጠቃላይ የበርና የመስኮት ግዥ እንዲፈጸምላቸው በጠየቁን መነሻ የሲዝ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተጠየቀውን የበርና መስኮቶች መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩትን አቅራቢ ድርጅቶች በዚህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ግዥውን መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የመወዳደሪያ መስፈርቶች አሟልታችሁ እንድትወዳደሩ የሲዝ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ጥሪ ያቀርባል፡፡
በዚህ መሰረት የመወዳደሪያ መስፈርቶች፡-
በዘርፉ የተሰጠ በቤትና በቢሮ ዕቃ አቅራቢነት (በእንጨትና ብረታ ብረት ሥራ) ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ፤
-
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ፣
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያለው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /Vat/ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው።
- ህጋዊ የታደሰ የሰውነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ድርጅቱ የሚጠበቅባቸውን የመንግሥት ዕዳ ግብር የከፈሉና ግዴታቸውን የተሰጡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከሚመለከተው አካላት ጋር ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ከታወቀ ባንክ ኢንሹራንስ የ10, 000 (አስር ሺህ ብር) ሲፒኦ ፣ ሊተር ኦፍ ክሬዲት እንዲሁም እንደ ተጫራቾች ምርጫ በጥሬ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊ ለሚሆኑበት የቤትና የቢሮ ዕቃ አቅራቢዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ገንዘብ 10% የውል ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ወይም ኢንሹራንስ ለማስያዝ ፍቃደኛ የሚሆን ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፣
ማሳሰቢያ፡-
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናቶች አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው ባሉበት በፋይናስ ጽ/ቤት በግዥ ኬዝ ቲም ሥራ ክፍል ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የሥራ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ከሲዝ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ትችላላችሁ፣
- ተወዳዳሪ ድርጅቶች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ የንግድ ፍቃድና አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ኮፒ ይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ አለው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0477770620 ወይም 0911452713 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፣
የደ/ም/ኢት/ክ/መንግሥት የቤንች ሸኮ ዞን ሲዝ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት
