የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ አስመልክቶ በ250 ካ.ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ አንድ ዋና ክፍል ቤት እና ሰባት ክፍል ሰርቪስ የመኖሪያ ቤት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሣሽ አቶ አየናቸው ተቻለ እና በአፈ/ተከሣሽ ወ/ሮ ደስታ ኃ/ሚካኤል መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈ/ተከሣሽ ንብረት የሆነው በደ/ብርሃን ሪጅዮ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር በእምዬ ምኒሊክ ክፍለ ከተማ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ቀበሌ የሚገኘው ከምስራቅ የቦታ ቁጥር 19፣ ከምዕራብ ቁጥር 23፣ ከሰሜን መንገድ፣ ከደቡብ ቁጥር 22 መካከል የሚገኘውን በ250 ካ.ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ አንድ ዋና ክፍል ቤት እና ሰባት ክፍል ሰርቪስ የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ 2,169,632.02 /ሁለት ሚሊየን አንድ መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰላሣ ሁለት ብር ከዜሮ ሁለት ሣንቲም/ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ታህሣስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች የግምቱን መነሻ 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ የዋስትና ወረቀት ወይም በሰ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ለሀራጅ ባዩ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው ለፍርድ ማስፈፀሚያ ነው።
- ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሣይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሀራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡
- የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል፡፡
የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
