የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ከጥር 01/2018 እስከ ሰኔ 30/2018 ድረስ ለ6 ወርየሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት እንዲሁም/ወይም ጥሬ እህል፣ የማጣፈጫ፣ ፉርኖ ዱቄት፣ የማገዶ እንጨት፣ ሱካር፤ እና ሸቀጣ ሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2
የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ከጥር 01/2018 እስከ ሰኔ 30/2018 ድረስ ለ6 ወርየሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት እንዲሁም/ወይም ጥሬ እህል፣ የማጣፈጫ፣ ፉርኖ ዱቄት፣ የማገዶ እንጨት፣ ሱካር፤ እና ሸቀጣ ሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማህበራትም ሆነ ግለሰብ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያ ማሟላት አለባቸው፡፡
1. በንግድ ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስከር ወረቀት ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡ የግብር ከፋይነት (TIN NO.) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ወይም የቫት ከፋይነት እንዲሁም የምዝገባ ምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዞኑ ማረሚያ ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየርላይ ውሎ በ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የህግ ታራሚዎች ኮሚቴ የማረሚያ ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ እና ከዞኑ አቃቤ ህግ ቢሮ እንዲሁም ከዞኑ ገ/ኢ/ትብብር በሚወከሉ በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መስሪያ ቤቱ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
5. በበሰለ ምግብ አቅርቦት በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
6. ጥሬ እህል ለማቅረብ ለሚወዳደሩ የእህሉን ናሙና እና የሚወዳደሩበትን አይነት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለጨረታው ያቀረቡት ሀሳብ መቀየር ወይንም ማሻሻል እንዲሁም ከጨረታው እራስን ማግለል አይችልም፡፡
8. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት አንስቶ ብ3ቀን ውስጥ ማረሚያ ቤት በመቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ የመጠቀም መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. የበሰለ ምግብ ለማቅረብ ያሸነፈው ማህበር ወይም ግለሰብ ጥራቱን የጠበቀና ለአንድ ሰው የሚሆን ማረሚያ ቤቱ ባወጣው ሜኑ መሰረት አቅርቦት መመገብ አለበት፡፡
10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞኑ ማረሚያ ቤት በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
11. ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያውና የውል ማስከበሪያ በጥቃቅንና አነስተኛ ደንብ 192/2009 ተሻሽሎ በወጣው አንቀፅ 27 መሰረት ከአደራጁ ክፍል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
12. ግለሰብም ሆነ ድርጅት ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያውን 2% በጥሬ ገንዘብ (በባንክየተመስከረለት CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለውል ማስከበሪያ 10% በጥሬ ገንዘብ (በባንክ የተመሰከረለት CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
13. ምግቡ የሚዘጋጀው በመስሪያቤቱ ማብሰያ ውስጥ ሆኖ በማብሰያ የሚያገለግሉ ዕቃዎች የማረሚያ ቤቱ እንዳለ ሆኖ የጎደለውን ጨረታውን ያሸነፈው ማህበራት ወይም ግለሰብ የማሟላት ግዴታ አለበት፡፡
14. ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከታች በተገለፀው አድራሻችን ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
15. ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ ካላቸው ለመ/ቤቱ ለበላይ አካሎች ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ እስከ 5ቀን ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ ይችላል፡፡
16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የደ/ም/ሸ/ዞን/ገ/ኢ/ልማት/ትብብር ፅ/ቤት ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-341-1190 011341-00-23 የደ/ም/ሸ/ዞን/ማረሚያ ቤት
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት
