ድርጅታችን ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለሠርግ አዳራሽ የሚሆኑ ክብ 60 ጠረጴዛ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Hope Enterprise University College (ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ፈቃድ አግኝቶ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጀሞ አካባቢ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት ላይ የሚገኝ የትምህርት ተቋም ነው።
በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት ለሠርግ አዳራሽ የሚሆኑ ክብ 60 ጠረጴዛ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም አምራች / አቅራቢ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ጀሞ 1 ለቡ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከሚገኘው የድርጅታችን ፋይናንስ ቢሮ በአካል መጥታችሁ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን አናሳውቃለን።
አጫራቹ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 09 74 17 66 00 ወይም 09 74 17 66 17
