ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የተለያየ ዓይነት ንብረት ለማጓጓዝ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት ውል አስሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
SUR Construction PLC (ሱር ኮንስትራክሽ ኃላ.የተ.የግ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የተለያየ ዓይነት ንብረት ለማጓጓዝ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት ውል አስሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች (ተወዳዳሪዎች) ከታች የተገለጸውን መስፈርት በማሟላት በጨረታ እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 13/04/2018 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ዝርዝር መስፈርት የያዘውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል አዲስ አበባ ሜጋ ህንፃ አጠገብ ከሚገኘው መስሪያ ቤታችን 15ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1502 ሎጅስቲክስ ዲፓርትመንት እንዲሁም መቐለ ላጪ የሚገኘው መ/ቤታችን 5ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 73 81 10 62፣ 09 10 87 98 42 ወይም 09 10 33 28 05 በመደወል ወይም በአካል በመሄድ መጠየቅ ይቻላል።
ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ.የተ.የግ.ማህበር
