ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የስራና ክህሎት ቢሮ ዳውሮ ዞን ዛባጋዞ ወረዳ የቃራዎ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ቀሪ ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የሥራና ክህሎት ቢሮ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የስራና ክህሎት ቢሮ ዳውሮ ዞን ዛባጋዞ ወረዳ የቃራዎ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ቀሪ ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት፡-
1. የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ምዝገባ ሴርትፍከት እና የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የግንባታ ስራ ደረጃ BC/GC 5 እና ከዛ በላይ መልካም ስራ አፈጻፀም ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾች የ500,000 ብር /አምስት መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ህጋዊ ር ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ሰነድ የማይመለስ 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል በቢሯችን ግ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ማግኘት ይቻላል።
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ሰላሳ ተከታታይ ቀን ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል።
6. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ሞልተው ኦርጅናሉንና አንዱን ኮፒ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ30 /ሰላሳ/ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን በቢሯችን ግን አስር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 07 ማስገባት ይቻላል።
7. ጨረታው ከ31ኛ /ሰላሳ አንደኛ/ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባይገኙም በተባለው ሰዓት ይከፈታል።
9. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን ይከፈታል።
10. ቢሮ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 10 የተጠቀሱ የጨረታ መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ ጨረታ እንዲወጣ እንጠይቃለን።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የሥራና ክህሎት ቢሮ
