Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም መስተዳደር ዞን የብቸና ከተማ አስተዳደር
  • Address በምስራቅ ጎጃም ዞን ብቸና ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 665 0030
  • Website
  • Deadline12 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Securityየተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከ15% /አስራ አምስት ፐርሰንት ያላነሰ
  • opening date2025-12-12 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም መስተዳደር ዞን የብቸና ከተማ አስተዳደር ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ፣ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለንግድና ለመኖሪያ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም መስተዳደር ዞን የብቸና ከተማ አስተዳደር


 

የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

 

  1. አድራሻ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም መስተዳደር ዞን የብቸና ጌታ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ፣ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለንግድና ለመኖሪያ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።

ስለዚህ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

  1. የጨረታ ቁጥር ብቸ/16/2018
  2. ጨረታ ዙር 16ኛ
  3. የጨረታው አይነት መደበኛ ጨረታ
  4. የመ/ቤት ስም ብቸና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
  5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ እና በማስታወቂያ ሰሌዳ ከተለጠፈበት ቀን ባሉት 10/ አስር/ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል። የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው በእለቱ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ይሆናል።
  6. ጨረታው የሚከፈተው ከጨረታው የመጨረሻ ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ብቸና ከተማ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ /ትልቁ አዳራሽ/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከተመሰከረለት ባንክ የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከ15% /አስራ አምስት ፐርሰንት ያላነሰ CPO /ሲፒኦ/ ማቅረብ ይኖርበታል።
  8. አሸናፊው ተጫራች ካቀረበው አጠቃላይ የሊዝ ዋጋ ለመኖርያና ለንግድ ቦታ ከ15% /አሥራ አምስት ፐርሰንት/ ያላነሰ ቅድመ ክፍያ ማቅረብ አለበት።
  9. ተጫራቹ የዋጋና የሃሳብ ማቅረቢያ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላት፡ - ኦርጅናል ሲፒኦ እና የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ በአንድ ፖስታ፣ የተሞላውን አንድ ኦርጅናል ሰነድ በአንድ ፖስታ፣ አንድ የተሞላ ኮፒ ሰነድ በአንድ ፖስታ በማሸግና ሦስቱን ፖስታዎች በአንድ ላይ በሌላ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በታሸገው ኢንቨሎፕ ፖስታ ላይ የተጫራቹን ስም፣ የቦታውን ልዩ ኮድ እና የጨረታ ቁጥር በግልጽ በመጻፍ ለቦታው በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገልጸው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል።
  11. ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  12. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ሲፒኦ የሚመለስበትን ጊዜ የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል።
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በ 058 665 0030/003/1092 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም መስተዳደር ዞን የብቸና ከተማ አስተዳደር

 

Save Tender