የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/ የግል ማህበር የተለያዩ ፕሪንተሮች እና አክሰስ ፖይንት (Printers, scanners, patch cord and Wireless access points) ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ተፈልጓል።
Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/12/2018
የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/ የግል ማህበር የተለያዩ ፕሪንተሮች እና አክሰስ ፖይንት (Printers, scanners, patch cord and Wireless access points) ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ተፈልጓል።
በዚህም፡-
ሎት1፡- ፕሪንተሮች እና አክሰስ ፖይንት (Printers, scanners, patch cord and access points) ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ወይም የአገልግሎቱ ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4:30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የደርጅቱ
ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
