በጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለየዩ አገልግሎቶችን ለ2018 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/2018 ዓ.ም.
በጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለየዩ አገልግሎቶችን ለ2018 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1፡- የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 2፡- የመኪና እቃ
- ሎት 3፡- የደንብ ልብስ
- ሎት 4፡- የመኪና ጥገና
- ሎት 5፡- ዘር
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን፤ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ፖስታ ላይ ለየትኛው እቃ ወይም አገልግሎት እንደሚወዳደሩ በግልጽ ለይተው መጻፍ አለባቸው።
- ተጫራቾች በመንግስት ግዢ ኤጀንሲ ድረ ገጽ (ዌብ ሳይት) ላይ በዘርፉ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ላይ ወይም አገልግሎቶች ሳምፕል ወይም ናሙና ለመስሪያ ቤቱ በማቅረብ የጥራትና የቴክኒክ ኮሚቴዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ይገመግማሉ።
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ የተዘረዘሩት እቃዎች ላይ የቀረበውን እስፔሲፊኬሽን በመሰረዝ በመደለዝ ማሻሻያ ማድረግና መለወጥ አይችሉም።
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጃችሁ ተጫራቾች ካደራጃችሁ አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆኑን ወይም ዋጋው ከቫት ውጪ መሆኑን በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው። ይህ ባይሆን ዋጋው ቫት ያከተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ ለሎት 1፡- 10,000፣ ለሎት2፡- 10,000፣ ለሎት3 10,000፣ ለሎት4፡- 20,000፣ ለሎት 5-10,000 እና የጠቅላላ ዋጋ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዶች በሙሉ በኤንቨሎፕ ታሽገው ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለየብቻው በማድረግና በማያያዝ ፊርማቸውንና ማህተማቸውን በፖስታዎች ላይ በማኖር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል በስራ ሰዓት ጉለሌ ክፍለ ከተማ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15 የጉ/ክ/ከ/አ የዲዛይን ና ግንባታ ስራዎች ፑል የአስ/ፋይ/ጽ/ቤት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የካፒታል መጠናቸው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በላይ የሆኑ ተጫራቾች ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ጊዜ የሚያበቃው የስራ ቀን ከሆነ በ10 ተከታታይ ቀናቶች በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆንን እየገለጽን ጨረታው አየር ላይ በዋለ 11ኛው ቀን ባለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4:30 በጉ/ክ/ከ/የዲ/ ግ /ስ/ ፑል የአስ/ፋይ/ፅ/ቤት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናሉ።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ባይሆን ከጨረታ ይሰረዛሉ።
- ተጫራቾች በንግድ ፈቃዳቸው በስተጀርባ ላይ የተዘረዘሩትን የንግድ ዘርፍ አይነቶች ኮፒ አድርገው ማቅረብ አለባቸው። የተጫራቾች ማህተም እና የንግድ ፍቃዳቸው እንዲሁም የደረሰኛቸው ስያሜ አንድ አይነት መሆን ይኖርበታል።
- በጨረታ መወዳደሪያ የሚያቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር ውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ባይሆን ግን በጨረታ የስያዙት /ሲፒኦ/ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የእቃ ብዛት ቀንሶ ወይም ጨምሮ ከአሸነፈው ድርጅት የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ የተዘረዘሩት እቃዎች ላይ የቀረበውን እስፔሲፊኬሽን በመሰረት ናሙና ወይም ሳምፕል ማስገባት ይኖርበታል።
ማሳሰቢያ፡-
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ጉለሌ ክ/ከ ዲዛይን ና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
በስልክ ቁጥር 011-8 12 10 96
በጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
