በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት አላቂ የቢሮ መገልገያ ዕቃ ማለትም ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ግዥ በጨረታ ዋጋ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የቢሮ መገልገያ ዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት አላቂ የቢሮ መገልገያ ዕቃ ማለትም ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ግዥ በጨረታ ዋጋ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- አግባብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና የዘመኑን ወይም 2018 ዓ.ም ግብር የነበሩበት ማረጋገጫ ያለው ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የ2017 ዓ.ም የግብር ከሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ጊዜው ያላለፈበት በአቅራቢነት በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግስት መ/ቤት የተሠጠ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት አሪጅናል ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 30,000 ከታወቀ ባንክ /C.P.O/ ማስያዝ የሚችል
- የውል አፈፃፀም ዋስትና ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 10% በጥሬ ወይም ከታወቀ ባንክ የተሰጠ CPO/ማስያዝ የሚችል
- ማንኛውንም ወጪዎች ማለትም የጉምሩክ የትራንስፖርት የባንክ እና የሌሎች አገልግሎት ወጪዎችን በራሱ ሸፍኖ ዕቃውን ማሰረከብ የሚችል
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የዕቃዉን ዝርዝር ወይም ስፔስፍኬሽን በተዘጋጀዉ የጨረታ ሠነድ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ያቀረቡት ናሙና ወዲያው ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በመክፈል እና ሰነዱን በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነዱ ላይ የአንዱን ዋጋ ብቻ ቫትን አካቶ በመሙላት ቴክኒካል ዶክመንት እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እንዲሁም ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒው ለየብቻ በማድረግ በአንድ ፖስታ አሽጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሳጥን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒና ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መምሪው በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ሌላው ተጫራች ተንተርሶ መጫረት አይችልም፡፡
- የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም
- ጨረታው መክፈቻ በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
