የምዕራብ ጉጂ ዞን ከፍተኛ የፍትሐብሔር ችሎት ስማቸው ከዚህ በታች የተጠቀሱት በከሳሽና ተከሳሽ መካከል ያለውን ክርክር አስመልክቶ ምዕራብ ጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰሌዳ ቁጥር ኦሮ 4582 የሆነ ትራከር ታዛቢዎች ባሉበት ጠዋት 5፡00-8፡00 ሰዓት በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በምዕራብ ጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የፍትሐብሄር ጉዳዮች ችሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
የአፈፃፀም ከሳሽ፡- ሲንቄ ባንክ መልካ ሶዳ ቅርንጫፍ
የአፈፃፀም ተከሳሽ፡- 1ኛ ሰለሞን አዶላ እና ታምራት ማህበር
2ኛ :- መልካ ሶዳ ወረዳ አስተዳደር
መካከል ያለውን ክርክር አስመልክቶ ምዕራብ ጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰሌዳ ቁጥር ኦሮ 4582 የሆነ ንብረትነቱ የ1ኛ የአፈፃፀም ተከሳሽ ሰለሞን አዶላ እና ታምራት ማህበር የሆነ የእዳ አፈፃፀም ውሳኔ ጠቅላላ ብር 5,093,137.52 (አምስት ሚሊዮን ዘጠና ሶስት ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት ብር ከሀምሳ ሁለት ሳንቲም) ከሳሽ ስለጠየቀ የሚሸጥ ስለሆነ ከዚህ በላይ የተገለፀው ትራክተር መነሻ ዋጋ ብር 4,781,374.05 /አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሰባ አራት ብር ከ 05 ሳንቲም/ በመያዝ 1ኛ ጨረታ ከቀን 18/03/2018 ዓ.ም እስከ ቀን 03/04/2018 ዓ.ም አስራ አምስት ቀን ከቆየ በኋላ በ 04/04/2018 ዓ.ም ትራክተሩ ወደ ሚገኘበት ቦታ ታዛቢዎች ባሉበት ጠዋት 5፡00-8፡00 ሰዓት መካከል ጨረታ በመከፈት ከተወዳደሪዎች ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ሽያጩን ማካሄድ ይፈልጋል፤ ስለዚህ በዚህ ጨረታ ማንኛውም መሳተፍ የሚፈልግ በተባለው ቀን እና ሰዓት በመገኘት መሳተፍ የሚችል መሆኑን ጨረታውን ያሸነፈው አካል ከጠቅላላ ክፍያ 25% ወዲያውኑ የሚከፍል ሲሆን ሙሉ ክፍያ ጨረታው ከተፈጸመ ቀን ጀምሮ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ የጨረታው አሸናፊ መብቱን በማሳጣት አዲስ ጨረታ ማስታወቂያ በድጋሚ የሚወጣ መሆኑን ተረድታችሁ ተወዳደሪዎች ጨረታ ላይ የተጋበዛችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በምዕራብ ጉጂ ዞን ከፍተኛ የፍትሐብሔር ችሎት
