የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ በህክምና ኮሌጁ ውስጥ አገልግሎት የሚሰጥ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች CBC or Hematology Analizer Machine፣ OR Liyht፣ Electro Surgical Machine /Cautery Machine for Major Operation Department/፣ ለደምብ ልብስ አገልግሎት የሚሆኑ ጨርቃ ጨርቆች እና አልባሳት፣ ለውሃ ቧምቧ የሚሆኑ የመለዋወጫ ዕቃዎች እና የኤሌክትሪክ መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ለመድኃንት ክፍል የሚሆን የመድኃኒት መደርደሪያ በአሉምኒየም ብረት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Yirgalem Medical college (የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 2/2018 በጀት ዓመት
የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ በህክምና ኮሌጁ ውስጥ አገልግሎት የሚሰጥ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች CBC or Hematology Analizer Machine፣ OR Liyht፣ Electro Surgical Machine /Cautery Machine for Major Operation Department/፣ ለደምብ ልብስ አገልግሎት የሚሆኑ ጨርቃ ጨርቆች እና አልባሳት፣ ለውሃ ቧምቧ የሚሆኑ የመለዋወጫ ዕቃዎች እና የኤሌክትሪክ መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ለመድኃንት ክፍል የሚሆን የመድኃኒት መደርደሪያ በአሉምኒየም ብረት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታውን መወዳደር የሚፈልጉ
- ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፤ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ብቻ ማስያዝ ወይንም ማቅረብ/ የሚችሉ፤
- በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸውን ማስረጃ ከገቢዎች ቢሮ የተሰጣቸውን የታደሰ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃዳቸውን፤ ተ.እ.ታ የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይ/ዓለም ሆስፒታል ህከምና ኮሌጅ ግዥ ንብ አስ ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ሁለት ቴክኒካል ኮፒ፣ አንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ሁለት ፋይናንሻል ኮፒ ሰነድ እያንዳንዱ ፖስታዎች በሰም ታሽጎ እና በትልቅ ፖስታ አንድ ላይ ተደርገው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሰነድ በተጫራቶች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ እና ቁልቁል ተደምሮ ህጋዊ የሆነ የድርጅቱ ማህተም በማሳረፍ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 6፡30 /ስድስት ሰዓት ተኩል/ ድረስ ይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6:30 /ስድስት ሰዓት ተኩል/ ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በግልፅ ይከፈታል፡፡
- የወቅቱ የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ መያዝ አለበት።
- አሰሪው መስርያ ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰብያ
- ተጫራቾች የባንክ ጋራንቲም ሆነ የኢንሹራንስ ዋስትና ማቅረብ የለባቸውም፡፡
- መ/ቤቱ እንዲያቀርቡ የሚፈለገው CPO እንዲሆን ብቻ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0926523944/ 0966901681 መደበኛ 0911708366 ይደውሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ
