በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የዲላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በስሩ ለሚያስገነባቸው የመንገድ መሰረተ ልማት እና ድልድዮች ለሰርቪስ አገልግሎት የሚውሉ በሎት 1- የአይሱዙ መኪና ኪራይ እና በሎት 2- የውሃ ቦቴ ኪራይ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን የዲላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የዲላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በስሩ ለሚያስገነባቸው የመንገድ መሰረተ ልማት እና ድልድዮች ለሰርቪስ አገልግሎት የሚውሉ በሎት 1- የአይሱዙ መኪና ኪራይ እና በሎት 2- የውሃ ቦቴ ኪራይ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤ የታደሰ የንግድ ስራ ወይም የአገልግሎት ስራ ፍቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የመንግስት መ/ቤቶች በሚያወጣቸው ጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቬሎፕ የፋይናንሺያል ፕሮፖዛሉን እና ቴከኒካል ዶክመንቱን በተለያየ ፖስታ በማሸግ አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ “ኦሪጂናል” እና “ኮፒ” በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውንም በተለያየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ የሚችሉት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15/አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ (ቅዳሜ እሁድ እና የህዝብ በዓላትን ጨምሮ) ሲሆን በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ይታሸጋል፤ጨረታው በዛው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥው የሥራ ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከዲስትሪክቱ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው አይሱዙ መኪኖች ሞዴላቸው 2008 እና ከዛ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው አይሱዙ መኪኖች እና የውሃ ቦቴዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ በጨረታ ሰነዶች ውስጥ አካተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ያቀረቧቸው ተሽከርካሪዎች ባለቤት ካልሆኑ የኪራይ ውል ስምምነት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ለኢትዮጵያውያን አቅራቢዎች ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋውን 1% የጨረታ ማስከበርያ በዲላ እና አካባቢው ባሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ጋራንቲ በባንክ በተረጋገጠ ከጨረታ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበርያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመርያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከጨረታ ደንብና መመርያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ ውል መግባት ይኖርበታል፡፡ ውሉን ካልገባ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆንና እድሉ ሁለተኛ ለወጣው ተጫራች ይሰጣል፡፡
- ዲስትሪክት መ/ቤቱ የተሻለ እድል ካገኝ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን የስልክ አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ስልክ ቁጥር :-0461317355//0906467741//0912015055 ዲላ ኢትዮጵያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን የዲላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
