Tender Detail

Tender Details

  • Company የጋሞ ገበሬዎች አትክልትና ፍራፍሬ ግብይት ሕብረት ሥራ ዩኒየን
  • Address ሲቀሳ፤ አ/ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጎን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-881-1445
  • Website
  • Deadline04 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price600.00
  • Bid Security300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-04 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

የጋሞ ገበሬዎች አትክልትና ፍራፍሬ ሕብረት ሥራ ዩኒየን በደቡብ ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር እና በአሌ ዞን ባሉት ወረዳዎች ለአርሶ አደሮች በያዝናቸው ምርት ዘመን 2018 ዓ.ም አ/ምንጭ፤ ከተማ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለጣቢዎች ለበጋ መስኖ፣ ለበልግና መኸር የአፈር ማዳበሪያ DAP/NPSB /ምጥን/ እና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

የጋሞ ገበሬዎች አትክልትና ፍራፍሬ ግብይት ሕብረት ሥራ ዩኒየን


 

የደረቅ ጭነት ማመላለሻ የጨረታ ቁጥር 007/2018

 

የጋሞ ገበሬዎች አትክልትና ፍራፍሬ ሕብረት ሥራ ዩኒየን በደቡብ ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር እና በአሌ ዞን ባሉት ወረዳዎች ለአርሶ አደሮች በያዝናቸው ምርት ዘመን 2018 ዓ.ም አ/ምንጭ፤ ከተማ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለጣቢዎች ለበጋ መስኖ፣ ለበልግና መኸር የአፈር ማዳበሪያ DAP/NPSB /ምጥን/ እና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፍለ የንግድ ፍቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ ያላት እና ከተደራጁበት አካባቢ ከገቢዎች የተሠጠ ክሊራንሱ ያለው/ያላት መሆን አለበት
  2. ከሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ መንግሥታዊ አካል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  3. ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ሥራን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ሁለትና ከዚህ በላይ ማቅረብ የሚችል፤
  4. የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ወይም ማራገፊያ ጣቢያ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ (C.P.O) ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈፀሙ በፊት ያሸነፈበትን ጭነት ማጓጓዝ ዋጋ ፐርሰንት ለውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ያስይዛል፤
  7. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ቢያስ 2,400 ኩ/ል (ሁለት ሺህ አራት መቶ ኩንታል) በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችል መኪኖችን የሠለዳ ቁጥር፤ የመኪና ዓይነት እና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግሥታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸውል፣
  8. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዘጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በመክፈል ከጋሞ ገበሬዎች አትክልትና ፍራፍሬ ግብይት ህብረት ሥራ ዩኒየን ዋና ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል፤
  9. የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል፡፡
  10. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ7 ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 8ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
  11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ሲቀሳ፤ አ/ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጎን

ስልክ 046-881-1445/0930003217/0911963268/0967000718

ፋክስ:- 046-881-3817

E.mail:-gamogofaunion@gmail.com

 

የጋሞ ገበሬዎች አትክልትና ፍራፍሬ ግብይት ሕብረት ሥራ ዩኒየን

 

 

Save Tender