በሲ/ብ/ክ/መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ከጥር 30/2018 እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ድረስ ለ6(ስድስት) ተከታታይ ወራት የሚቆይ ለህግ ታራሚዎች የተለያዩ ምግብ ማጣፈጫዎች እና ምግብ ማብሰያ የማገዶ እንጨት ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተመለከቱትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም
የግዥ ጨረታ ቁጥር 02/2018
በሲ/ብ/ክ/መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ከጥር 30/2018 እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ድረስ ለ6(ስድስት) ተከታታይ ወራት የሚቆይ ለህግ ታራሚዎች የተለያዩ ምግብ ማጣፈጫዎች እና ምግብ ማብሰያ የማገዶ እንጨት ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተመለከቱትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
መስኪያ |
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
መስኪያ |
|
1 |
ዛላ በርበሬ(ያልተፈጨ) |
በኩ/ል |
9 |
ሠፌድ |
በቁጥር |
|
2 |
የምግብ ጨው |
በኩ/ል |
10 |
ካሜራ 500 ግራም |
በፓኬት |
|
3 |
ጎመን ዘር |
በኩ/ል |
11 |
እርድ |
በኩ/ል |
|
4 |
ቀይ ሽንኩርት |
በኩ/ል |
12 |
ቃሪያ |
በኪ/ግ |
|
5 |
ነጭ ሽንኩርት |
በኩ/ል |
13 |
በቀርከሀ የተሰራ አክምባሎ |
በቁጥር |
|
6 |
ዝንጅብል |
በኩ/ል |
14 |
በፍልጥ የተዘጋጀ የማገዶ እንጨት |
በሜ/ክብ |
|
7 |
ሻይ ቅጠል ባለ 80 ግራም |
በካርቶን |
15 |
በግንዲላ የተዘጋጀ የማገዶ እንጨት |
በሜ/ክብ |
|
8 |
የእንጀራ ምጣድ |
በቁጥር |
16 |
ምስር |
በኩ/ል |
ህጋዊ ተወዳዳሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈለጋል።
ስለዚህ ጨረታው የሚካሄድበት የሥራ ቋንቋ አማርኛ ሲሆን በሚወዳደሩበት የንግድ ሥራ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤የግብር ከፋይነት ማስረጃ ያላቸው፤ የዘመኑን የግብር የከፈሉና ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፤ በተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡ፤ በጨረታ መወዳደር የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት ዝርዝር ለመመዝገባቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የያዘ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉና በጨረታ የተጠቀሱ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል የጨረታውን ሠነድ ከይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ገዝተው ከሞሉ በኃላ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ አሥራ አምስተኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ድረስ የታሸገውን ኤንቬሎፕ ወደ ጨረታ ሳጥን አስጉበተው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡35 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኃላ በዕለቱ ከቀኑ 8፡40 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ይከፈታል። ጨረታውን ሰነድ ለውድድር አቅርበው ከግል ፍላጎታቸው /ሁኔታ/ የተነሳ በዕለቱ የማይገኙ ሲሆን ጨረታው ተከፍተው ውጤቱ ይገለጽላቸዋል እንጂ የጨረታውን ሂደት የሚያስተጓጉል ነገር አይኖርም። አንድ ተጫራች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይቻልም። በጨረታው ሠነዱ የተመለከቱትን ዓይነቶች ከላይ በሰንጠረዥ ውስጥ የተገለጸው መሰረት ይሆናል። የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸ ጊዜ ጅምሮ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ አቅርበው ውል መፈጸም አለባቸው። አሸናፊዎችን አሸናፊነታቸውን እንደተገለጸ ውል የማይፈጽሙ ሲሆን ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ አይመለስም(ይወረሳል)። የጨረታው ዝርዝር በጨረታው የአፈጻጸም መመሪያ ላይ የተግለጸ ስለሆነ በይበልጥ ተቀባይነት ያለው የጨረታ ሰነድ በመሆኑ አንድ በአንድ ማንበብ ይኖርባቸዋል። ጨረታ አውጪው መ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046-225-24-03 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም
